የደሬቴድ ዲጂታል ሚዲያ የሐምሌ 19/2015 ዓ.ም የዕለቱ ዋና ዋና ዜናዎች፡-
👉የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀዊያ ብሄራዊ ፈተናን አስጀመሩ፡፡
👉ውስን መሬት ላላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች የተሻሻሉ የእንስሳትና የዶሮ ዝርያዎችን ተደራሽ በማድረግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተሠራ መሆኑን የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለጹ።
👉የኢትዮጵያ በግጭት ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎች መልሶ የማልማት ፕሮጀክት አቢይ ኮሚቴ ለ2016 የበጀት ዓመት በግጭት ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች ለመልሶ ማቋቋምና ግንባታ ተግባር የሚውል የ60 ሚሊዮን ዶላር በጀት አጸደቀ፡፡
👉ዓመታዊ የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በሀዋሳ ከተማ ደብረ ምህረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ቤተክርስቲያን በድምቀት ተከበረ።
👉የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን በማጠናከር ከ51 ሺህ በላይ ሴቶችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የደቡብ ኦሞ ዞን ሴቶች ሊግ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
👉በ2015 በጀት ዓመት ከየካቲት ወር ጀምሮ ወደተለያዩ አፍሪካ ሀገራት 62,846 የከብት ቆዳ በመላክ 405,542 ዶላር ገቢ መገኘቱን በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የቁም እንስሳትና እንስሳት ተዋጽኦ የወጪ ንግድ ዴስክ ኃላፊ አቶ አበበ ታደሰ ገለጹ፡፡
👉የሲዳማ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት “ነገን ዛሬ እንትከል” በሚል መሪ ሀሳብ አረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በሀዋሳ ከተማ ቱላ ክፍለ ከተማ ኤሬዶ ተራራ ላይ አከናወነ።
👉የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎትን ያካተተው የልዑካን ቡድን በኬንያ ከሚገኙ ከተለያዩ የኮምዩኒቲ ማህበራት አደረጃጀት ተወካዮች፣ ባለሃብቶች፣ የሙያ ማህበራትና የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መሪዎች ጋር በናይሮቢ ውይይት አካሄደ።
More Stories
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በጌዴኦ ዞን ሁሉም ትምህርት ቤቶች በተለያዩ ኩነቶች ተከበረ
የሁሉን አቀፍ የገጠር ተደራሽ መንገድ ልማት ማጠናከር የክልሉ የመልማት አቅም ከፍ ያደርጋል – የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባስጀመረው የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ ያተኮረ ውይይት መካሄድ ጀመረ