የባስኬቶ ዞን ሽግግር ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤ እያካሄደ ነው
በአስቸኳይ ጉባኤው በነበረው የግማሽ ቀን ውሎ የዞኑን ዋና አስተዳዳሪን ጨምሮ ልዩ ልዩ ሹመቶችን መርምሮ አጽድቋል።
የባስኬቶ ዞን ሽግግር ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤው ኢንጂነር በዛብህ ገበየሁን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
ዋና አስተዳዳሪው በምክር ቤቱ ፊት ባደረጉት ንግግር እንዳሉት፤ በተግባር የተደገፈ የዕድገት ጉዞን በማፋጠን የዞኑን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ለማድረግ በቁርጠኝነት ይሠራል።
የወጣቶችና ሴቶችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ በማድረግ የዜጎችን እኩል ተጠቃሚነት ይበልጥ እንደሚረጋገጥ አብራርተዋል።
የግብርና ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ቴክኖሎጅዎች አጠቃቀም ውስንነት መኖር እና የኢንዱስትሪዎች በበቂ ሁኔታ ካለመስፋፋት የተነሳ ለብዙ ወጣቶች የሥራ እድል መፍጠር እንዳልተቻለ አንስተዋል።
በማህበራዊ ዘርፍ የትምሀርት ጥራት፣ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትና ርካታ፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች አሁንም መሻሻል ይፈልጋሉ ብለዋል።
ዋና አስተዳዳሪው የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው እንዲያገለግሉ ያቀረቧቸው አቶ ክንፉ ሻቦ እና ምክትል አስተዳዳሪና ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ሠላምነሽ ጌታቸው (ዶ/ር) እንዲሁም የሌሎችም አስተባባሪ ኮሚቴዎች ሹመት በምክር ቤቱ አባላት ተተችቶ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።
ዘጋቢ: አወል ከድር – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
ችግሮች በመቋቋም በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈፃጸም መመዝገቡን በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የጂንካ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ
የሴቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነትንና ተሳትፎን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
መንግስት ለትምህርቱ ዘርፍ የሰጠውን ትኩረት ሁሉም ያለ ስስት ሊደግፍ እንደሚገባ ተገለጸ