የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በኮንሶ ዞን ካራት ከተማ እያካሄደ ይገኛል

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በኮንሶ ዞን ካራት ከተማ እያካሄደ ይገኛል

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ ዳርጌ ዳሼ በመክፈቻ ንግግራቸው እንዳሉት፤ 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ነፃ ገለልተኛና ፍፁም ሠላማዊ ሆኖ የተጠናቀቀበት መሆኑን ተከትሎ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶችን ለመፍታት ኢትዮጵያዊያን እየመከሩ ባሉበት ወቅት መሆኑ ጉባኤውን ልዩ ያደርገዋል።

በብሔሮች መካከል ያለው አንድነት ተጠናክሮ እዲቀጥል ብዝሃነት ማንነት ያለን በመሆኑ ለሀገራችን ምሳሌ በሚሆን መልኩ ማፅናት ይገባል ብለዋል።

ምክር ቤቱ በርካታ ባህሎችን፣ ቋንቋዎችንና ዕሴቶችን አጉልቶ በማውጣት የኢኮኖሚ ምንጭ እንዲሆን በቀጣይ ይሰራል ያሉት ምክትል አፈ ጉባኤው፤ ብዝሃነታችን የሆነውን ህብረብሔራዊ አንድነታችንን የበለጠ ለማጠናከር በህዝቦች መካከል መተማመን እንዲፈጠር ከማድረግ አኳያ ስራዎች በትኩረት መሠራታቸውን ገልፀዋል።

በተለይ የሠላምና የፀጥታ ስራዎችን ዘላቂ ከማድረግ አንፃር ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መሠራቱንም አመላክተዋል።

ስለዚህ ብሔር ብሔረሰቦችን ተጠቃሚ ለማድረግ ምክር ቤቱ ለኢንሼቲቦች ተግባራዊነት ትኩረት መስጠቱን ጠቁመው ሁሉም እንዲረባረቡም ምክትል አፈ ጉባኤው አባስበዋል።

ዘጋቢ፡ ፀሐይ ጎበና – ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን