በተቀናጀ የመሬት አያያዝና አጠቃቀም የአርሶ አደሩን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

በተቀናጀ የመሬት አያያዝና አጠቃቀም የአርሶ አደሩን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የFULOR ETHIOPIA ፕሮጀክት በተቀናጀ የመሬት አያያዝና አጠቃቀም የአርሶ አደሩን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

‎በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም UNDP የአየር ንብረት ለውጥና የአከባቢ ጥበቃ ዩኒቲ አስተባባሪ ወይዘሮ ውቧ መኮንን የተመራው ልዑክ በክልሉ ጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ በተቀናጀ የመሬት አያያዝና አጠቃቀም ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራትን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል።

‎እንደ አውሮፒያኑ የዘመን ቀመር በ1965 የተቋቋመ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም UNDP በዓለም 170 በላይ አገሮችና ግዛቶች ውስጥ ከመንግሥታት፣ ከማህበረሰቦች እና ከሌሎች አጋሮች ጋር በመተባበር በተለያዩ የልማት ሥራዎች ላይ ተሰማርቶ ይገኛል።

‎ድርጅቱ በድህነት ቅነሳ፣ ዘላቂ ልማት ማስፋፊያ፣ በአየር ንብረት ለውጥ የሚመጡ አደጋዎችን መቋቋም በሚያስችሉ እና የሴቶችና ወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በትኩረት የሚሰራ መሆኑን በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም የአየር ንብረት ለውጥ እና የአከባቢ ጥበቃ ዩኒት አስተባባሪ ወይዘሮ ውቧ መኮንን አስታውቀዋል።

‎በኢትዮጵያም UNDP ከመንግሥትና ከተለያዩ አጋሮች ጋር በመሆን በድህነት ቅነሳና ኢኮኖሚያዊ ልማትን እንዲሁም የአካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥን ተከትሎ የሚመጣ የአደጋ መከላከልና መቋቋም ላይ ከመስራቱም ባሻገር የወጣቶችና የሴቶች አቅም ማጎልበት በሚችሉ ዘርፎች ላይም በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

‎በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የፍሎር ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ አለምበጁ ክፍሌ በበኩላቸው FULOR ፕሮጀክት በክልሉ በቆየባቸው ሁለት ዓመታት በክልሉ በተቀናጀ የመሬት አያያዝና አጠቃቀም የአርሶ አደሩን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ውጤታማ ተግባራትን ማከናወን መቻሉን አስረድተዋል።

‎ በሁለት ዓመት ቆይታው በፕሮጀክቱ የተከናውኑ ተግባራት ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም በመጡ አስተባባሪዎች እየተገበኘ መሆኑን ያስረዱት አለምበጁ በይርጋጨፌ ወረዳ በነበራቸው ቆይታም የአርሶ አደሩን የሴቶችንና የወጣቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተከናወኑ ሥራዎች ደስተኛ መሆናቸውን ማረጋገጥ መቻሉን አስረድተዋል።

‎አቶ ዳዊት ቡኔ የይርጋጨፌ ወረዳ አስተዳዳሪ ሲሆኑ FULOR ETHIOPIA በወረዳው አምስት በሚሆኑ ቀበሌዎች በቡና ፣ እንሰት እና የደን ሀብት ልማት ላይ ላለፉት ሁለት ዓመታት ከአከባቢው ህብረተሰብ ባለፈ የመንግስት አጋዥ ሀይል በመሆን አመርቂ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን አስረድተዋል።

‎ዘጋቢ : ሳሙኤል በቀለ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን