አሌሃንድሮ ጋርናቾ ከቼልሲ ጋር ያለው የወደፊት ዕጣ ፈንታ በአጣብቂኝ ውስጥ
የቼልሲው አጥቂ አሌሃንድሮ ጋርናቾ ክለቡን በዘንድሮው የዝውውር መስኮት የመልቀቅ እድሉ እየሰፋ መምጣቱን ተከትሎ፣ የዝውውሩ ሂደት የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ትኩረት ሆኗል።
ሰማያዊዮቹ ጋርናቾ በክለቡ ውስጥ ለቋሚ አሰላለፍ ዋስትና መስጠት ስለማይችሉ ተጫዋቹ በቋሚነት እንዲሸጥ ይፈልጋሉ።
ክለቡ በተጫዋቹ ዝውውር ላይ 50 ሚሊዮን ዩሮ እንደታመነበት ተዘግቧል።
የጣሊያኑ ክለብ ሮማ ጋርናቾን ለማስፈረም በመፈለግ ድርድር ቢጀምርም፣ በብድሩ ሁኔታ ላይ እስካሁን መግባባት እንዳልቻለ ተነግሯል።
ሮማ አርጄንቲናዊውን ተጫዋች በውሰት የማስፈረም ፍላጎት ያለው ሲሆን ቼልሲ ግን ተጫዋቹን በቋሚ ዝውውር የመልቀቅ ፍላጎት ብቻ እንዳለው ተገልጿል።
ጋርናቾ በአሁኑ ሰዓት ከሮማ በተጨማሪ ከእንግሊዝ፣ ከጣሊያን እና ከሳውዲ አረቢያ ክለቦች ከፍተኛ ፍላጎት እየተደረገበት ይገኛል።
ጋርናቾ አሁን ላይ ከምዕራብ ለንደኑ ክለብ ጋር ለመለያየት የዝውውር ሂደት ላይ ሙሉ ትኩረት በማድረጉ ምክንያት፣ እስካሁን ወደ ልምምድ አለመመለሱን የመረጃ ምንጮች ይገልጻሉ።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
“ኤርሊንግ ሀላንድን አምበል የምናደርገዉ ከሆነ ትልቅ ችግር ዉስጥ እንገባለን” ኤንዞ ማሬስካ
ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ጆርጂና ሮድሪጌዝ የጋብቻ ስነ ስርዓታቸውን ፈፀሙ
ሶማሊያዊው ዳኛ ኦማር አርታን የዩኤፋ ሱፐር ካፕን በዋና ዳኝነት በመምራት የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሊሆኑ ነው