አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ በሪያል ማድሪድ ስራቸውን ጀመሩ
አንጋፋው እና ስኬታማው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ፣ ለሁለተኛ ጊዜ የሪያል ማድሪድ ዋና አሰልጣኝ በመሆን ስራቸውን በይፋ ጀምረዋል።
ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ከሪያል ማድሪድ ጋር የሶስት ዓመት ኮንትራት መፈራረማቸው ይታወሳል።
ይህ ሹመት በተለይ የክለቡ ደጋፊዎችና የስፖርት ቤተሰቡ በጉጉት ሲጠብቁት የነበረ ሲሆን፣ የቀድሞ አሰልጣኙ ወደ ዋና ከተማዋ መመለስ የክለቡን ቀጣይ ጉዞ በተስፋ የተሞላ አድርጎታል።
ይህ የሞሪንሆ ሁለተኛ የሪያል ማድሪድ ቆይታ፣ የመጀመሪያው የኃላፊነት ጊዜያቸው ካበቃበት 13 ዓመታት በኋላ የተከናወነ ነው።
በወቅቱ በሳንቲያጎ ቤርናቤው በነበራቸው የሶስት ዓመት ቆይታ፣ የክለቡን ታሪክ በወርቅ ቀለም አስመዝግበዋል።
ባሳለፉት ስኬታማ ጊዜ ፡ የሊጉን ዋንጫ በሪከርድ ነጥብ ማሳካት ችለዋል።
በተጨማሪም የሀገሪቱን የጥሎ ማለፍ ዋንጫ ወደ ማድሪድ አመጥተዋል።
አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ፣ ከዚህ ቀደም የነበራቸውን ልምድና ስኬት በመያዝ፣ ሪያል ማድሪድን በአውሮፓ እና በስፔን የላቀ ደረጃ ላይ ለማድረስ ዳግም መነሳታቸው በእግርኳሱ አለም ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል።
የሪያል ማድሪድ ደጋፊዎች “ልዩው ሰው” (The Special One) ወደ ቡድኑ መመለስ፣ በቡድኑ ላይ ምን አይነት ለውጥ እንደሚያመጣ በከፍተኛ ጉጉት ይጠባበቃሉ።
ዘጋቢ ፡ ሙሉቀን ባሳ
አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ በሪያል ማድሪድ ስራቸውን ጀመሩ

More Stories
ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ሲዳማ ቡናን በማሸነፍ የኢትዮጵያ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነ
ማርከስ ራሽፎርድ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ይመለሳል
የሜሲ እንባ