በ2018 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ሲዳማ ቡናን 2ለ0 በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ሻምፒዮን ሆኗል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ለወልዋሎ የማሸነፊያ ጎሎችን ኮንካኒ ሀፊዝ እና ተቀይሮ ወደ ሜዳ የገባው በየነ ባንጃው ከመረብ አሳርፈዋል።
በአሰልጣኝ ግርማ ታደሰ የሚመራው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ በቀጣይ ኢትዮጵያን ወክሎ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ይሳተፋል።
የፕሪምየር ሊጉ ሻምፒዮን ሲዳማ ቡና በበኩሉ በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የሚሳተፍ ይሆናል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ሲዳማ ቡናን በማሸነፍ የኢትዮጵያ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነ

More Stories
ካርሎስ ባሌባ ለማንቼስተር ዩናይትድ ፊርማውን አኖረ
አርሰናል ከ ላምፓርዱ ኮቨንተሪ ሲቲ
አርሰናል ኤዝሪ ኮንሳን በ55 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ አስፈረመ