በበጀት አመቱ 98ሺህ 200 ቶን የኢንዱትሪ ማእድንና 13ሺህ 110 ቶን ሜትር ኪዩብ የኮንስትራክሽን ማእድን ማምረት መቻሉ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ሰኔ 26/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በበጀት አመቱ በማእድን ዘርፍ 98ሺህ 200 ቶን የኢንዱትሪ ማእድንና 13ሺህ 110 ቶን ሜትር ኪዩብ የኮንስትራክሽን ማእድን በማምረት ለኢንዱስትሪ ግብአት ማቅረብ መቻሉን የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማእድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን መኔዶ አስታወቁ።
ኤጀንሲው የ2018 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2019 በጀት አመት እቅድ ላይ የሚመክር የውይይት መድረክ በወልቂጤ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማእድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን መኔዶ በዚህ ወቅት አንዳስታወቁት በበጀት አመቱ በማእድን ዘርፍ 98ሺህ 200 ቶን የኢንዱትሪ ማእድንና 13ሺህ 110 ቶን ሜትር ኪዩብ የኮንስትራክሽን ማእድን በማምረት ለኢንዱስትሪ ግብአት ማቅረብ መቻሉን ጠቁመው፥ በዘርፉ ከ9ሺህ 800 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ እድል መፈጠሩን አስረድተዋል።
በምክክር መድረኩ ላይ የኤጀንሲው የ2018 እቅድ አፈፃፀምና በ2019 የቀጣይ የእቅድ አቅጣጫዎች ዙሪያ ውይይት ይደረጋል።
በመድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የመሠረተ ልማት ጉዳዮች አማካሪ አቶ መዝረዲን ሁሴንን ጨምሮ በክልሉ ከሁሉም መዋቅሮች የተወጣጡ የዘርፉ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ዘጋቢ፡ አስቻለው ተስፋዬ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
የሀለባ ዞን ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከ3 ቢልዮን 293 ሚልዮን ብር ባለይ በጀት አጸደቀ
መስራት እየቻሉ የገንዘብ እጥረት የገጠማቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ችግሮች ለመፍታት የህብረት ስራ ማህበራት ሚና ቀላል አለመሆኑ ተገለጸ
በስልጤ ልማት ማህበር ለ3ኛ ጊዜ በተዘጋጀው የችግኝ ተከላ መርሀግብር ከሀገር ውስጥና ከውጪ ሀገር የተሰበሰቡ የአካባቢው ተወላጆች በዞኑ በሚገኙ የላንፉሮ ወረዳና ጦራ ከተማ አስተዳደር ችግኞችን ተክለዋል ።