ሳንቲ ካዞርላ ከእግርኳስ ተጫዋችነት ራሱን አገለለ
የቀድሞ የአርሰናል አማካይ ሳንቲ ካዞርላ ከእግርኳስ ተጫዋችነት ራሱን ማግለሉን ይፋ አድርጓል።
25 ዓመታትን በተጫዋችነት ያሳለፈው ካዞርላ በ41 ዓመቱ ነው ራሱን ከእግርኳስ ተጫዋችነት ያገለለው።
ሳንቲ ካዞርላ በተጫዋችነት ዘመኑ በክለብ ደረጃ ለአርሰናል፣ማላጋ፣ቪያሪያልን፣ሪያል ኦቬዶ እና አል ሳድ ተጫውቶ አሳልፏል።
በብሔራዊ ቡድን ደረጃ ደግሞ ለስፔን 81 ጨዋታዎችን አከናውኖ 15 ጎሎችን በስሙ አስመዝግቧል። ሁለት የአውሮፓ ዋንጫዎችንም ከላሮጃዎች ጋር ማንሳት ችሏል።
ሳንቲ ካዞርላ ያለፉትን ሦስት ተከታታይ የውድድር ዓመታት በልጅነት ክለቡ ሪያል ኦቬዳ ሲጫወት መቆየቱ አይዘነጋም።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
ሳንቲ ካዞርላ ከእግርኳስ ተጫዋችነት ራሱን አገለለ

More Stories
ካርሎስ ባሌባ ለማንቼስተር ዩናይትድ ፊርማውን አኖረ
አርሰናል ከ ላምፓርዱ ኮቨንተሪ ሲቲ
አርሰናል ኤዝሪ ኮንሳን በ55 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ አስፈረመ