በክልሉ በመስኖ ልማት ዘርፍ ቀጣይነት ያለው ዕድገት ማስመዝገብ እንዲቻል ስትራቴጂካዊ አቅድ ተነድፎ እየተሰራ ነው
ሀዋሳ፡ ሰኔ 25/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በክልሉ በመስኖ ልማት ዘርፍ ቀጣይነት ያለው ዕድገት ማስመዝገብ እንዲቻል ስትራቴጂካዊ አቅድ ተነድፎ እየተሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ካሳዬ ተክሌ(ኢ/ር) ገለፁ፡፡
ኤጀንሲው በአማካሪው ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቀረበውን የክልሉን የመስኖ አቅም ስትራቴጂ ጥናት የባለድርሻ አካላት በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ እየገመገመ ይገኛል።
ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ካሳዬ ተክሌ(ኢ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት እንደ ሀገር ብሎም እንደ ክልል በመስኖ ልማት ዘርፍ በዘመናዊ መንገድ ብዙ እንዳልተሰራ አስታውሰው ከለውጡ በኋላ ግን ብዙ ጥረቶች እንዳሉ አመላክተዋል።
በዚህም በክልሉ በመስኖ ልማት ዘርፍ ቀጣይነት ያለው ዕድገት ማስመዝገብ እንዲቻል ስትራቴጂካዊ አቅድ ተነድፎ እየተሰራ ነው።
የኦሞ ጊቤ ተፋሰስና በሪፍት ቫሊ የተደረገ ጥናት ቢኖርም በክልሉ በአስሩም መዋቅሮች ላይ በሁሉም መስክ በመሬቱም፣ በውሃ ሀብቱ ለመስኖ ልማት የሚውለውን አቅም ለመለየት አስቸጋር እንደነበረ ጠቅሰው፥ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ጋር ውል በመግባት ጥናት ሲደረግ እንደነበር ዋና ዳይሬክተሩ አንስተዋል።
በዛሬው ዕለት በዝርዝር የሚቀረቡ የጥናት ውጤቶች ላይ ሳይንሳዊና ሙያዊ ሀሳብ መስጠት ለማዳበር የሚያስችል ዓላማ ያደረገ መድረክ መሆኑንም አመላክተዋል።
በምክክር መድረኩ ላይ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የርዕሰ መስተዳድሩ የመሠረተ ልማት ጉዳዮች አማካሪ አቶ መዝረዲን ሁሴን፣ የክልሉ የማዕድንና ኢኔርጂ ልማት ኤጂንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መኮንን መኔዶን ጨምሮ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ መምህርና የጥናት ቡድኑ መሪ ፕሮፈሰር አለማየሁ ሙሉነህና ሌሎች በጥናቱ ላይ የተሳተፉ ምሁራን እና እንዲሁም ከዞንና ከልዩ ወረዳ የተውጣጡ የዘርፉ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ዘጋቢ፡ ተዘራ በቀለ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
የሀለባ ዞን ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከ3 ቢልዮን 293 ሚልዮን ብር ባለይ በጀት አጸደቀ
መስራት እየቻሉ የገንዘብ እጥረት የገጠማቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ችግሮች ለመፍታት የህብረት ስራ ማህበራት ሚና ቀላል አለመሆኑ ተገለጸ
በስልጤ ልማት ማህበር ለ3ኛ ጊዜ በተዘጋጀው የችግኝ ተከላ መርሀግብር ከሀገር ውስጥና ከውጪ ሀገር የተሰበሰቡ የአካባቢው ተወላጆች በዞኑ በሚገኙ የላንፉሮ ወረዳና ጦራ ከተማ አስተዳደር ችግኞችን ተክለዋል ።