በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 1.5 ሚሊዬን ዜጎችን ለማሳተፍ መታቀዱ ተገለጸ

በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 1.5 ሚሊዬን ዜጎችን ለማሳተፍ መታቀዱ ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ሰኔ 19/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በ2018 በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 1.5 ሚሊዬን ዜጎችን ለማሳተፍ መታቀዱን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ።

የ2017 ክልላዊ የክረምት ወራት የወጣቶች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት መዝጊያና በ2018 ዓመተ-ምህረት መነሻ ዕቅድ ዙሪያ የምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ገነት መኩሪያ ባስተላለፉት መልዕክት በዘንድሮ ክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 1.5 ሚሊዬን ዜጎችን ለማሳተፍ መታቀዱን አስታውቀዋል።

በ2017 በዘርፉ ታቅዶ በተሰራ ስራ ክልሉ ተሸላሚ እንደነበር አስታውሰው ወጣቶችን በዚህ አገልግሎት ከማሳተፍ ባሻገር የዘርፉ በተሰሩ ስራዎች በማህበረሰቡ ውስጥ ባህል እየሆኑ መምጣታቸውን ተናግረዋል።

ባለፈው ዓመት 1 ሚሊዬን 300 ሺህ ማህበረሰብ አካላትን በማሳተፍ 2 ሚሊዬን 200 ሺህ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አንስተዋል።

በዚህም 1.1 ቢሊዬን ብር የሚገመት ሀብት በማሰባሰብ የመንግስትን በጀት ማትረፍ መቻሉን ተናግረዋል።

ለ2018 ዓ.ም ዕቅድ ለማሳካት በቅንጅት እንደሚሰራ ጠቁመው፥ ባለድርሻ አካላት ተግባራትን በትኩረት ማከናወን እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የአፈጻጸምና የቀጣይ አቅጣጫ ጠቋሚ ሰነዶች በቢሮው ባለሙያዎች እየቀረበ ነው።

ዘጋቢ፡ ሀብታሙ ኃይሌ – ከቦንጋ ጣቢያችን