በግብርናው ኢኮኖሚ ዘርፍ ትልቅ ፋይዳ እያስገኘ ያለውን የእንስሳት ሀብት ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሠራ ነው – የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር መሠረት አበራ
በግብርናው ኢኮኖሚ ዘርፍ ትልቅ ፋይዳ እያስገኘ ያለውን የእንስሳት ሀብት ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን በሀዲያ ዞን ግብርና መምሪያ
የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር መሠረት አበራ ገለጹ፡፡
የእንስሳትን ሀብት ውጤታማ ለማድረግ በሚደረገው ርብርብ የመኖ ዝግጅት ጉልህ ድርሻ እንዳለው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀዲያ ዞን ግብርና መምሪያ አስገነዘበ፡፡
በዞኑ ከ24 ሺህ 6 መቶ ሄክታር በላይ ማሳ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ባላቸው የእንስሳት መኖ ሣር መሸፈኑም ተጠቁሟል።
በግብርናው ኢኮኖሚ ዘርፍ ትልቅ ፋይዳ እያስገኘ ያለውን የእንስሳት ሀብት ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑንም በሀዲያ ዞን ግብርና መምሪያ የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር መሠረት አበራ ገልጸዋል።
ዘርፉ በምግብ ዋስትና፣ በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በኢንዱስትሪና በወተት ምርቶች ሰፊ ስራዎችን እየሠራ ነው ያሉት ዶክተር መሠረት፤ በዚህ ወቅትም የእንስሳትን ዝርያ ከማሻሻል ባለፈ በእንስሳት ጤና አጠባበቅ እና በመኖ ዝግጅት በተከናወነው ተግባር ውጤት መመዝገቡን አስረድተዋል።
የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ በእንስሳት መኖ ዝግጅት ላይ ትኩረት ማድረጉን የገለፁት ኃላፊዋ፤ በበጀት ዓመቱ 24 ሺህ 8 መቶ 18 ሄክታር መሬት የእንስሳት መኖ ሣር ለማልማት ከታቀደው 24 ሺህ 6 መቶ 15 ሄክታር ማልማት መቻሉን አስታውቀዋል።
ለወተት ምርት፣ ለድለባና ማሞከት እንዲሁም ለንብ ማነብ የሚያገለግሉ የተለያዩ የመኖ ዝርያዎችን ለአርሶ አደሮች በማስተዋወቅና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በማቀናጀት የሳር ዘር አቅርቦት ስራ መሰራቱንም ዶክተር መሠረት ገልጸዋል።
እነዚህ ለእንስሳት መኖነት የሚያገለግሉ የሳር ዓይነቶች ድርቅን የሚቋቋሙና ለመሬት ለምነትም አበርክቶ ያላቸው መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡
በዞኑ ከ40 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ዘመናዊ የመኖ ሳር በማምረት ተጠቃሚ መሆናቸውን የጠቆሙት ዶክተር መሠረት፤ አርሶ አደሩ የእንስሳት መኖ በስፋት በማምረት ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆንም መክረዋል።
በሴክተሩ የእንስሳት መኖ አዘገጃጀት ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ፀደቀ ዘውዴ በበኩላቸው፤ አርሶ አደሩ ከገለባ፣ ከድርቆሽ፣ ከኢንደስትሪ ግብዓቶች፣ ከዘመናዊ የሳር ዓይነቶች መኖ በማዘጋጀት እንስሳትን መንከባከብ ያስፈልገዋል ብለዋል።
አክለውም ለእንስሳት የመመገቢያ ገንዳ በማዘጋጀትና በመመገብ የመኖ፣ የጊዜና የጉልበት ብክነትን መታደግ እና የእንስሳትን ጤናና ደህንነት መጠበቅ እንደሚቻልም አቶ ፀደቀ አስገንዝበዋል።
በዞኑ ሌሞ ወረዳ ሹርሞ ቀበሌ ከሚገኙ አርሶ አደሮች መካከል አቶ ደገፈ አቦዬ እና አቶ ደመቀ ወዕለሞ፤ በእንስሳት መኖ አዘገጃጀት ዙሪያ ትምህርት ካገኙ ወዲህ የተለያዩ የመኖ ሳሮችን በመትከልና እንስሳትን በመንከባከብ የተሻለ የወተት ምርት እያገኙ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡ መንግሥቱ ፊጣሞ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
የቡና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ የኣሪ ዞን ግብርና መምሪያ ቡናና ቅመማ ቅመም ጽህፈት ቤት አሰታወቀ
በሀገሪቱ ያለው 80 በመቶ ቡና ያረጀ በመሆኑ መታደስ እንደሚገባ ተጠቆመ
የብራይት ፕሮጀክት የሴቶችንና ህፃናትን የስራ ጫና ከማቃለል ባሻገር የንፁህ መጠጥ ውሀ ተደራሽነት ላይ የሚመታይ ተግባር ማከናወኑን የጋሞ ዞን ውሀና ኢነርጂ መምሪያ አስታወቀ