የቡና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ የኣሪ ዞን ግብርና መምሪያ ቡናና ቅመማ ቅመም ጽህፈት ቤት አሰታወቀ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኣሪ ዞን ግብርና መምሪያ ቡናና ቅመማ ቅመም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጋናክሽ አርዳክ እንደገለጹት፤ በዞኑ ባሉ ወረዳዎች የሚገኘውን የቡና ምርታማነትን በተሻለና በጥራት ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
አንደ ዞን የቡና ሽፋን 30 ሺህ 257 ሄክታር ከነበረበት ወደ 40 ሺህ ሄክታር ለማድረሰ እየተሠራ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፤ ወደ ማዕከላዊ ገበያ 2 ሺህ 4 መቶ ቶን ለመላክ ታቅዶ 1 ሺህ 8 መቶ ቶን በመላክ የዕቅዱን 83 በመቶ ማሳካት መቻሉን ገልጸዋል።
እንደ ዞን 3.1 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በሁለት ዙር ለመትከል ዝግጅት ከተደረገው 2.5 ሚሊዮን ችግኝ እየተተከለ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፤ ቀሪው ከፊታችን ባሉ ወራት ተግባራዊ እንደሚደረግ ገልፀዋል።
የዎባ ኣሪ ወረዳ አርሶ አደር አካባቢ የቡና ሽፋን መጠኑ 8 ሺህ ሄክታር መሆኑን የገለጹት የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ቡናና ቅመመ ቅመም ኤክሰቴሽን ኃላፊ አቶ አስተዋይ ታምሩ፤ በቀጣይ ክረምት በተመረጡ ቦታዎች ላይ ከ75 ሺህ በላይ ችግኝ ለመትከል ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን ተናግረዋል።
ያረጀ ቡናን ነቅሎ በአዲስ መልክ የመተካት ስራ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ገልጸዋል ኃላፊው፡፡
ምርቱን በአግባቡ እንዲጠቀሙ በተፈጠረው የግንዛቤ ትምህርትና ቀደም ሲል ባላቸው ልምድ መሠረት የቡና አረምን በተገቢው መንገድ በማረምና በመንከባከብ የተሻለ ውጤት እያገኙ መሆናቸውን የተናገሩት አርሶ አደር አቶ ቦጋለ ጋልሶ ናቸው።
ዘጋቢ: ፍቃዱ ግዲ – ከጂንካ ጣቢያችን
የቡና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ የኣሪ ዞን ግብርና መምሪያ ቡናና ቅመማ ቅመም ጽህፈት ቤት አሰታወቀ

More Stories
በሀገሪቱ ያለው 80 በመቶ ቡና ያረጀ በመሆኑ መታደስ እንደሚገባ ተጠቆመ
የብራይት ፕሮጀክት የሴቶችንና ህፃናትን የስራ ጫና ከማቃለል ባሻገር የንፁህ መጠጥ ውሀ ተደራሽነት ላይ የሚመታይ ተግባር ማከናወኑን የጋሞ ዞን ውሀና ኢነርጂ መምሪያ አስታወቀ
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጥናታቸው በተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ላይ ያተኮረ የማረጋገጫ ወርክሾፕ እና የርክክብ መርሃ ግብር እያካሄደ ይገኛል