ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ቡናን በማሸነፍ የሊጉ ሻምፒዮን ለመሆን በእጅጉ ተቃረበ
ሀዋሳ: ሰኔ 07/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በ35ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ፥ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በቡና ደርቢ ኢትዮጵያ ቡና ከመመራት ተነስቶ 2ለ1 በማሸነፍ ሻምፒዮን ለመሆን በእጅጉ ተቃርቧል።
ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ለሲዳማ ቡና ወሳኝ የማሸነፊያ ጎሎችን ያሬድ ባየህ እና ብርሀኑ በቀለ አስገኝተዋል።
በጨዋታው ኢትዮጵያ ቡናን መሪ ማድረግ ችላ የነበረችውን ጎል ዘላለም አባተ አስቆጥሯል።
ብርሃኑ በቀለ 7ኛ የፕሪሚዬር ሊግ ጎሉን በዚህ ዓመት ለሲዳማ ቡና አስቆጥሯል።
ሲዳማ ቡና ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን 64 በማድረስ ከተከታዩ መቻል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 11 አድርሷል።
በአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ የሚመራው ሲዳማ ቡና በነገው ዕለት ነገሌ አሪሲ በሀዋሳ ከተማ የሚሸነፍ ከሆነ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የሊጉ ሻምፒዮን መሆኑን ያረጋግጣል።
በዛሬው ዕለት በተካሄደ ሌላ ጨዋታ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው መቻል በቅዱስ ጊዮርጊስ 3ለ0 ተሸንፏል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
“ማንቸስተር ሲቲ በዚህ አጨዋወት ሊጉን ማሸነፍ አይችልም”ፖል ሜርሰን
ኬሮድ የጎዳና ላይ ሩጫ ህዝብ ለህዝብ የሚያስተሳስርና አንድነታችንን ይበልጥ የምናጠናክርበት በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ
ከ1500 በላይ ኤሊት አትሌቶች የሚሳተፉበት 6ኛው ዙር የኬሮድ የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በወልቂጤ ከተማ ተጀመረ