በዘንድሮ የትምህርት ዘመን የተማዎችን ውጤት ለማሻሻል በተደረገው ጥረት የተሻለ ውጤት እንደሚጠበቅ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለፀ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ክልላዊና ሀገር አቀፍ ፈተናዎችን ለመስጠት የሚያስችል በቂ ዝግጅት ማጠናቀቁንም አስታውቋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ከትምህርት ባለድርሻዎች ጋር በቅንጅት በሰራው ስራ የተሻለ ውጤት እንደሚጠበቅ አመላክቷል፡፡
የክልሉ ትምህርት ቢሮ አጠቃላይ የትምህርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኢሳያስ እንድርያስ እንዳሉት ዘንድሮ 6ኛ፣ 8ኛ እና የ12ኛ ተማሪዎችን ክልላዊና ሀገር አቀፍ ፈተናዎች በወረቀት እና በበይነ መረብ አማካኝነት ለመስጠት የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ማጠናቀቁን ገልፀዋል፡፡
በዚህም 6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ሚኒስትሪ 126ሺ 226 ተማሪዎች፣ 86ሺ 447 የ8ኛ ክፍል እና የክልል አቀፍ ሚኒስትሪ 52ሺ 500 የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና የሚወስዱ መሆናቸውን የገለፁት ኃላፊው፥ ተማሪዎች ለማብቃት እና ዘንድሮ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ሰፊ ጥረት ተደርጓል ብለዋል፡፡
ኩረጃን ለማስቀረት ከዘንድሮ አስራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል ሰባ በመቶ የሚሆኑት በበይነ-መረብ በቀጥታ የሚፈተኑ መሆናቸውን ገልፀው፥ በቂ ዝግጅት መደረጉን አስረድተዋል፡፡
በክልሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተየ ያለው የፈተና ውጤት መሻሻል ተስፋ ሰጪ በመሆኑ ባለድርሻ አካላት ይበልጥ መትጋት ይገባቸዋል ነው ያሉት፡፡
የክልላዊና ሀገር አቀፍ ፈተናዎች ዝግጅታቸው አልቆ ተማሪዎች አሁን ላይ የሞዴል ፈተና እየተቀበሉ በመሆናቸውን ተናግረው፥ በሰኔ ወር የመጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ የሚሰጠው ፈተና በስኬት እንዲጠናቀቅ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ አቶ ኢሳያስ መክረዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ወልደገብርኤል ላቀው – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
ወጣቶች በሀገርና በሀገረ መንግስት ግንባታ በመሳተፍ ለሀገራቸው ያላቸውን ፍቅር መግለጽ እንዳለባቸው በቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን አማን ከተማ ወጣቶች ገለጹ
በሃይለማሪያምና ሮማን ፋዉንደሽን 297 ኢንተርፕራይዞችን በማደራጀት ወደ ሥራ ለማስገባት እየሰራ መሆኑን የወረዳው ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ገለጸ
2ኛው ዙር ዓለም አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መካሄድ ጀምሯል