“የምንኖረው በሀዘን እና በደስታ መካከል ነው”

በይበልጣል ጫኔ

ወላይታ ሶዶ ከተማ ተገኝተናል። የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ሰፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ ነን። የሆስፒታሉ ግቢ ንጹህ ነው። ህንፃዎቹም እንዲሁ ዓይነ ግቡ ናቸው።

ዘለቅን ወደ ውስጥ። ወደ አንዱ ጥግ÷ ቁርሳቸውን የሚቀማምሱ አስታማሚዎች ይታያሉ። ወደ ካርድ ክፍል፣ ወደ መድኃኒት ቤት፣ ወደ ምርመራ ክፍሎች እና መሰል ቦታዎች የሚንቀሳቀሱ ሰዎች÷ እዚህም እዚያም አሉ። የዛሬው እቱ መለኛ አምዳችን÷ በአንዲት ትጉህ ነርስ ህይወት ላይ ነው÷ ትኩረቱን ያደረገው።

በነርስነት ሙያ÷ ከባለሙያነት ጀምሮ በልዩ ልዩ ኃላፊነቶች ሰርታለች። በታካሚዎችም ሆነ በስራ ባልደረቦቿ በልዩነት ትወደዳለች። በተለየ ሁኔታ ችግር ካልገጠገማት በስተቀር÷ በፍፁም ከስራ ገበታዋ ላይ አትታጣም። ይህቺ ነርስ ሲስተር ፂዮን ሰለሞን ትባላለች። ሲስተር ፂዮን ትውልድ እና ዕድገቷ ሀዋሳ ነው።

በሃዋሳ ታቦር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና በሃዋሳ ታቦር አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርቷን ተከታትላለች። “ከተማሩ ወላጆች ነው የተገኘሁት”÷ የምትለው ሲስተር ፂዮን÷ ከዕድሜ እኩዮቿ እኩል ትምህርት ቤት ለመግባት አልተቸገረችም።

ነገር ግን ለቤተሰቦቿ ሁለተኛ ልጅ ብትሆንም÷ ቀዳሚዋ ሴት እርሷ በመሆኗ የቤት ውስጥ የስራ ጫና ነበረባት። “ከትምህርት ሰዓት ውጪ ቤተሰብን በስራ ማገዝ ሁሉም ቤት ያለ ተግባር ነው። ከዚያ ውጪ ግን እናቴ የመንግስት ሰራተኛ ስለነበረች÷ ታናናሽ እህቶቼን እንደ እናት የመንከባከብ ኃላፊነት ነበረብኝ።

ከትምህርት ቤት እኩል መጥተን ወንድሜ ወደ ጥናቱ ሲሄድ እኔ ወደ ማጀት ነበር የምገባው። እንደዛም ሆኖ ውጤቴ ጥሩ ነበር” የድሮው አስራ ሁለተኛ ክፍል የመጨረሻ ተፈታኝ ነበረች÷ ሲስተር ፂዮን። ወደ ዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ተፈትና ውጤት ብትጠብቅም ሳይመጣላት ቀረ። በዚህም ምክንያት ምንም እንኳን ፍለጎቷ ባይሆንም÷ ሃዋሳ መምህራን ኮሌጅ ገብታ ትምህርቷን መከታተል ጀመረች።

ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላም ተወዳድራ ስላለፈች÷ ወደምትወደው ሙያ የሚያመራትን መንገድ ፈልጋ ይርጋለም ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ገባች። “ይርጋለም ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እንደገባሁ”÷ አለች፦ “ይርጋለም ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እንደገባሁ÷ ዩኒቨርስቲ ገባለሁ የሚለው ምኞቴ ስላልተሳካ እና ቁጭት ስለነበረብኝ÷ የተሻለ ውጤት አምጥቼ ቤተሰቦቼንም ማስደሰት ስለምፈልግ በትኩረት ነበር ትምህርቴን የምከታተለው።

በዚያ ጊዜ በተለይ ከቤተሰብ እይታ ውጪ ሲኮን ለፈተና የሚዳርጉ በርካታ ነገሮች ነበሩ። ያንን ሁሉ ተቋቁሜ በጥሩ ውጤት በዲፕሎማ ተመረቅኩ” ሲስተር ፂዮን በተለይም የወጣትነት ዘመኗን አስታውሳ÷ የሴት ልጅ ህይወት በብዙ ፈተና ውስጥ ነው የሚያልፈው ትላለች። ከዕድሜ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ፆታዊ ፍላጎት፣ የአቻ ግፊት እና ሁሉን ነገር ሞክሬ ልየው የማለት ጉጉት÷ ከስኬት የሚያስቀሩ እንቅፋቶች ናቸው÷ እንደ ሲስተር ፂዮን ሃሳብ።

እሷ ግን ከተማሩ ወላጆች መገኘቷ እና ከቤተሰቦቿ ጋር ሁሉን ነገር በግልፅ መወያየት መቻሏ በህይወት መንገድ ላይ ከመደነቃቀፍ ታድጓታል። “በመንገድ ላይ የገጠመንን ሁሉ ለአባታችን እንነግረዋለን። በዚያ መነሻነት ይመክረናል። ‘አንዲት ሴት የራሷ የገቢ ምንጭ ከሌላት ትዳር ብትመሰርት እንኳን የባሏ ጥገኛ ነው የምትሆነው።

ነገ ከባሎቻችሁ የዕለት ወጪያችሁን የምትጠይቁ ዓይነት ሴቶች እንዳትሆኑ’ ይለን ነበር” ትላለች ትላንቷን አስታውሳ። በእርግጥም ይኼንን ሃሳብ ግዙፍ ነስቶ በዘመዶቿ አሊያም ባካባቢዋ ሰዎች ላይ አይታዋለች። የባሎቻቸው ጥገኛ ሆነው የኖሩ ሴቶች÷ ህይወት ምን ያህል አሰልቺ ሆኖባቸው እንደነበር ታውቃለች።

ለዚያም ይሆናል የአባቷን ምክር ያለአንዳች ማጓደል የምትቀበለው። ሲስተር ፂዮን በዚህ ልክ የአባቷን ምክር ትቀበል እንጂ÷ አስቦ እና አገናዝቦ ተገቢ በሆነ ዕድሜ ላይ የፍቅር ጓደኛ መያዝ አስፈላጊ ነው ብላ ታምናለች። “ከዛም ከዚህም ማለት ነው እንጂ መጥፎ አንድ የፍቅር ጓደኛ መያዝ አስፈላጊ ነው”÷ ትላለች የራሷን ህይወት አብነት በማድረግ።

እሷ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ተማሪ ሆና ነበር ፍቅረኛ የኖራት። ቅደሚያ በጓደኝነት÷ ቀጥሎም በትዳር እስከዛሬ አብረው አሉ። ሲስተር ፂዮን ከይርጋለም ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በዲፕሎማ እንደተመረቀች÷ አሁን ወደምትሰራበት ወደ ወላይታ ሶዶ ኮምፕሪሄንሲቭ ሰፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነው ያቀናችው። ወቅቱ 1999 ዓ.ም ነበር።

በዚያ ጊዜ አንድም ለስራው ትልቅ ጉጉት ስለነበራት÷ በሌላ መልኩም እንደ እሷ ወጣት እና አዲስ ተቀጣሪዎች ስለነበሩ ለመላመድ እምብዛም አልተቸገረችም። “የመጀመሪያዎቹን የስራ ዓመታቶቼን አብዝቼ ነው የምወዳቸው። ስራን ናፍቄ ነው የምሰራው። አዳር ተረኛ ስንሆን እስኪነጋ ድረስ አንዳችን ወደ ሌላችን እየሄድን እየተጋገዝን÷ ሰው ድኖ ሲወጣ እና አመሰግናለሁ ሲለን … በተለይ የመጀመሪያዎቹ አምስት ዓመታት ልዩ ነበሩ” ከዚያ በኋላ ያሉትን ዓመታት ሙያዊ ከሆነው አገልግሎት ባሻገር÷ በተለያዩ ኃላፊነቶች ነው ተቋሙን እያገለገለች የምትገኘው።

“በህክምና ሙያ ላይ ብዙ ዓይነት ሰው ነው ስናስተናግድ የምንውለው። ደስ ካለው ጋር ደስ ይለናል። ከሚያለቅሱት ጋር እናለቅሳለን። መድኃኒት መግዛት የሚያቅተው ይመጣል። ከራሳችንም ከስራ ባልደረቦቻችንም ለምነን መድሃኒት እንገዛለን። አንዳንድ ጊዜ የልጆቻችንን ወተት ሳይቀር ለታካሚ ይዘን የምንመጣበት ጊዜ አለ። ከአመራርነቱ በላይ በሙያዬ የሰራሁባቸውን አስር ዓመታት እወዳቸዋለሁ” ሲስተር ፂዮን ሰለሞን ለነርስነት ሙያ የተለየ ፍቅር አላት።

ሙያው በሷ ህይወት ውስጥ ያለውን ቦታ ለመግለፅ ሁሉ ትቸገራለች፦ “ነርስ መሆን ማለት ልዩ ነገር ነው። እንዴት ብዬ እንደምገልፀው አላውቅም። የሚከፈለን ደሞዝ አይደለም የኛ እርካታ። የሚሰጡን የተለያዩ ጥቅማጥቅሞች አይደሉም። ይሞታል ወይም ተስፋ የለውም የተባለ ሰው መጥቶ÷ ተረባርበን የእግዚአብሔር እገዛ ታክሎበት ሲድን ያ ነው የኛ እፎይታ።

ቤተሰብ እልል ሲል ሲደሰት ስናይ እሱ ነው የኛ ደስታ” ዛሬ ላይ የማዋለድ ስራ የሚሰሩት ሚድ ዋይፎች (አዋላጅ ነርሶች) ናቸው። ቀደም ባለው ጊዜ ግን ማዋለድም የነርሶች ተግባር ነበር። ታድያ በዚያ ጊዜ “አንዲት ሴት ምጥ ተይዛ ቤተሰብ እና ጎረቤት አጅቧት መጥታ÷ ከጭንቋ ስትገላገል ያለውን ደስታ ምድር ላይ ምንም አይተካውም” ትላለች። ሲስተር ፂዮን በሰራ በሳለፈቻቸው ዓመታት ብዙ ጊዜ ሃዘን እና ደስታ ተፈራርቆባታል። በተለይ በሙያዋ ስታገለግለው የነበረ ታካሚ ህይወቱ ሲያልፍ ከባድ ሃዘን ውስጥ ነው የምትገባው።

ጊዜ የገጠማት ግን ሁሌም የምትረሳው አይደለም፦ “ትንሽ ልጅ ነው። ዕድሜው ከስምንት ዓመት አይበልጥም። እኛ ያሰብነው እንደሚድን ነው። ቤተሰቦቹም የኛን ስሜት ተጋርተው÷ ይድናል የሚል ተስፋ ሰንቀው ነበር። ኦፕሬሽን ተሰርቶለት ቁስሉ ሳይድንለት ቀረና ሁለተኛ ገባ። ከሁለተኛው ኦፕሬሽን በኋላ ግን እየቀነሰ መጣ።

ያ ልጅ ሞቶ ቤተሰቦቹ ያደረጉት ነገር ሁሌም ያሳዝነኛል። እናንተም ያን ሁሉ ዋጋ ከፍላችሁ ልፋታችሁ መና ቀረ ሲሉ ነበር በሀዘን ሥሜት ውስጥ ሆነው የተናገሩት። ይህ ከሆነ ወደ አምስት ዓመት ቢሆነውም እስከዛሬ ግን ከውስጤ አይወጣም” የወላይታ ሶዶ ነዋሪ የሆነች አንዲት የኤች አይ ቪ ታማሚ ደግሞ የደስታዋ ምንጭ ሆናለች።

ይህቺ ሴት የመኖር ተስፋዋ ተሟጦ ነው ወደ ሆስፒታል የመጣችው። ራሷን መቆጣጠር አትችልም። ቤተሰቦቿም ትተርፋለች የሚል ሃሳብ አልነበራቸውም። ከአሁን አሁን ትሞታለች ተብላ እየተጠበቀች÷ በቀናት ውስጥ ለውጥ አመጣች። ከአንድ ወር በላይ በተደረገላት የህክምና ክትትል ድና ወደ ቤቷ ሄደች።

ይህቺ ታካሚ ከዚያ በኋላ አግብታ ልጅ ወልዳ የራሷን ስራ እየሰራች ነው የምትኖረው። አሁን ድረስ ከተማ ውስጥ ሳያት በጣም እደሰታለሁ÷ ያለችን ታታሪዋ ነርስ “ብዙውን ጊዜ በደስታ እና በሃዘን መካከል ነው የምንኖረው” ብላለች። ሲስተር ፂዮን ሰለሞን ዛሬ ላይ የነርሲንግ እና ሚድዋይፍርይ ዳይሬክተር ናት።

የኃላፊነትን መንገድ የጀመረችው÷ ኃላፊዎች ለተለያዩ ጉዳዮች ወጣ ሲሉ በውክልና እንዲሁም ትናንሽ ክፍሎችን በሃላፊነት በመምራት ነው። በተለያዩ ቦታዎች ላይ በኃላፊነት ስድስት ዓመታት ካገለገለች በኋላ ነው አሁን ወዳለችበት ደረጃ የተሸጋገረችው። “በፊት የነበርኩበት የኃላፊነት ቦታ የሪፖርት ስራ ስለሚበዛው ከሙያዊ ስራ አውጥቶኝ ነበር። ነገር ግን መረጃ ለመውሰድ ስመጣም የማየውን ነገር ቦታው ላይ ላሉ ሰዎች መጠቆም እወዳለሁ።

ምክንያቱም የኛ ስራ አለቃ ስለተቆጣጠረህ የምትሰራው ዓይነት አይደለም። ህሊናህ አዞህ ነው በዋናነት ልትሰራ የምትችለው” ትላለች። አሁን በያዘችው የኃላፊነት ቦታ በማገልገል ሦስተኛ ዓመቷን ይዛለች። ቀደም ሲል ቦታው ተይዞ የነበረው በስፔሻሊስት ሀኪም ነው። እነሱ ደግሞ አንድም ብዙውን ጊዜያቸውን ሰዎችን በማከም ስለሚያሳልፉ÷ በሌላ በኩልም የነሱን ትኩረት የሚፈልጉ ተማሪዎች እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

በአንጻሩ በበጀት ዓመቱ ለብዙ ዓመታት የመልካም አስተዳደር ችግር ሆነው የቆዩ ድልድዮች ተጠናቀው ለህብረተሰቡ ክፍት መሆናቸውንም አብራርተዋል፡፡ የተጀመሩ ስራዎችን ለማስጀመር ማሽነሪ እና የበጀት አቅም ስለሚፈልግ እንደ ክልልም ትኩረት ተሰጥቶበት ስራዎች መጀመራቸውን ነው ዋና አስተዳዳሪው የተናገሩት፡፡ በበጀት ዓመቱ ዞኑ ወደ አምስትና ከዚያ በላይ የቢሮ መሰረተ ልማት ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ነው የገለጹት፡፡

በወረዳም ይሁን በከተማ አስተዳደር የልማት ስራዎች ታቅደው በመንግስት በጀትና በህብረተሰብ ተሳትፎ እየተሰሩ መሆናቸውን ተናግረው፣ ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ ከመብራትም ጋር ተያይዞ የትራንስፎርመር ዝርጋታ ተደራሽ ባልሆኑ አካባቢዎች የማድረስ ስራዎች መሰራታቸውን ነው ዋና አስተዳዳሪው የተናገሩት፡፡

በዞኑ የኔትወርክ ሽፋን ያልደረሰባቸው በርካታ ቀበሌያት አሉ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በኢትዮ ቴሌኮም የሚሰሩ ስራዎች ዙሪያ ጥናት እየተደረገ መሆኑን ዶክተር ጌትነት ገልጸዋል፡፡ ከማህበራዊ ዘርፍ አኳያ ትምህርትና ጤና ቁልፍ ሴክተሮች ሲሆኑ ትምህርት ላይ እንደ ሀገር የጥራት ችግር መኖሩን፣ በዞኑም ይህ ችግር ተስተውሏል ነው ያሉት። ችግሩን ለመፍታት ባለድርሻ አካላትን በማወያየትና ተማሪዎችን በማሳተፍ ለተማሪዎች ውጤታማነት የተለያዩ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ጠቁመዋል፡፡

ትምህርት ቤቶችን ከማጠናከር አንፃር ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት በበጀት ዓመቱ ጅምሩ ጥሩ ሆኖ ጥራት እንዲመጣ በዞኑ ልማት ማህበር አማካይነት ሞዴል ትምህርት ቤት ተገንብቶ ተማሪዎችን የማስተማር ስራዎች ተጀምረዋል ብለዋል፡፡ በዚህም ከተለያዩ ትምህርት ቤቶችና ወረዳዎች ከፍተኛ ነጥብ ያላቸው ተማሪዎች ተለይተው እንዲማሩ መደረጉን አስረድተዋል። ከጤና አኳያም ተቋማትን ማጠናከር እና አገልግሎትን ውጤታማ ማድረግ በተለይም ሆስፒታሎች ላይ ቁሳቁስ ለማሟላት ጥረት መደረጉን ነው የተናገሩት፡፡

የደም አቅርቦት በጤና ተቋማት እንደ ችግር ስለሚነሳ ከሳውላ አርባምንጭና ወላይታ ሶዶ የሚኬድ በመሆኑ ችግሩን ለመቅረፍ ከክልሉ መንግስት ጋር በመነጋገር የደም ባንክ ግንባታ ስራው እየተጠናቀቀ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ ነገር ግን ማሽነሪና ለደም ባንኩ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን በቀጣይ ለማሟላት ጥረት እየተደረገ መሆኑን የሚናገሩት ዋና አስተዳዳሪው፣ በዚህም አንድም እናት በደም እጥረት ምክንያት እንዳትሞት ስራዎች በትኩረት መሰራታቸውንም አያይዘው ገልፀዋል፡፡

ይህም ስራ በዞኑ መንግስት ብቻ ሳይሆን ከክልልም አልፎ የፌደራል መንግስት ድጋፍ የሚፈልግ ጉዳይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በጤናው ዙሪያ ያለው ትልቁ ተግዳሮት ቅድመ መከላከል ወይም የጤና ኤክስቴንሽን ስራዎች ውጤታማ አለመሆናቸው ነው። ከዚህም ጋር ተያይዞ ተከስቶ የነበረውን የወባ እና የኮሌራ ወረርሽኞችን ለመቀልበስ ተችሏል፡፡ የገቢ እና የኢኮኖሚ አቅምን ከማሳደግ አንፃር ትልቁ ስራ ዞኑ ወጪውን በራሱ ገቢ መሸፈን አለበት ከሚል እሳቤ የገቢ አቅሙን 70 በመቶ ለማሳደግ መታቀዱን ተናግረው፣ ከዚህም አንፃር ከ748 ሚሊየን 378 ሺህ 414 ብር ከ76 ሳንቲም መሰብሰቡን ይገልጻሉ፡፡

ዞኑ ለዓለም ገበያ የሚቀርቡ እንደ ቡና ያሉ ምርቶችን ለማዕከላዊ ገበያ በማቅረብ ይታወቃል። በ2ዐ15 ዓመት 2 ሺህ ቶን ቡና ለማቅረብ መታቀዱንም ነው የተናገሩት፡፡ እስካሁንም 1 ሺህ 800 ቶን ቡና ስለመቅረቡ ይገልጻሉ፡፡ በአሪቲ ልማትም ዘንድሮ ለማዕከላዊ ገበያ ከ10 ሺህ ቶን በላይ ቀርቧል፡፡

ከዚህም ውስጥ 4 ሺህ 50 ቶን ለውጪ ገበያ መቅረቡን ነው የተናገሩት። ክልሉ በሰጠው ግብረመልስ የተሻለ ገቢ ለኢኮኖሚው አስተዋጽኦ አድርጓል ነው ያሉት፡፡ ሰሊጥንም ለውጪ ገበያ፣ እንዲሁም ኮረሪማ ለማዕከላዊ፣ ለሀገር ውስጥና ለውጪ ገበያ የማቅረቡ ስራዎች ስለተጀመሩ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስረድተዋል፡፡ የሳውላ ከተማ ከንቲባ አቶ ኤርሚያስ ስላሏቸው÷ ለቢሮ ስራ ያላቸው ትኩረት እምብዛም ነው። በዚህ መነሻነት ነርሶች በነርስ መመራት አለባቸው ተብሎ ነው÷ እሷ ወደ ኃላፊነት የመጣቸው። “እዚህ ስመጣ ነገሮች አስቸጋሪ ነበሩ።

በነርሲንግ ብቻ ከአራት መቶ በላይ ሰራተኛ ነው ያለው። ይኼንን ስታፍ የሚያስተባብሩ ደግሞ ወደ 38 የዲፓርትመንት ኃላፊዎች አሉ። በፊት የራሴ አለቃ ራሴ ነኝ። ሪፖርት ነበር በብዛት የማዘጋጀው። አሁን ደግሞ ለኔ ነው ሪፖርት የሚቀርብልኝ። በተለይ የመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት አስቸጋሪዎች ነበሩ። በዚያ ጊዜ ቤቱን ፈር ለማስያዝ የሰውነቴ ክብደት ሁሉ ቀንሷል” በእርግጥ ሲስተር ፂዮን ወደዚህ ኃላፊነት ከመጣች ጀምሮ በስሯ ካሉ ነርሶች አለባበስ ጀምሮ ብዙ ነገር ተለውጧል። ከሷ በታች ባሉ ደረጃዎች ላይ የሚገኙ የስራ ኃላፊዎችንም በማብቃት ረገድ ብዙ ስራዎች ሰርታለች።

በማንኛውም ሰዓት በቦታዋ ቢተኩ ያለአንዳች መደነቃቀፍ ስራቸውን እንደሚወጡም በኩራት ትናገራለች። ከሲስተር ፂዮን ሙሉጌታ ጋር አብረው ከሚሰሩ ባለሙያዎች አንዷ ናት። ሲስተር ሊሊ ላምቤቦ። የሆስፒታሉ ቀዶ ህክምና ክፍል የነርሶች አስተባባሪ ናት። ስለ ሲስተር ፂዮን ይህንን ብላናለች፦ “በሲስተር ፂዮን ስር ሆኜ ነው የአስተባባሪነት ስራዬን የምሰራው።

በቆይታዬ ከሷ በርካታ ተሞክሮዎችን ቀስሜያለሁ። በተለይም የምትሰጠው አመራር መልካም ነው። ሰራተኛ ሁሉ አንድ አይደለም። በአግባቡ ስራውን የማይሰራ ሰው ሲያጋጥማት ከአስተባባሪው ጋር አስቀምጣ መጀመሪያ በምክር ነው ልትመልሰው የምትሞክረው። በሂደትም የምትወስደው እርምጃ ሌላውን ሰራተኛ ጭምር የሚያስተምር ነው” በነገራችን ላይ ሲስተር ፂዮን የትምህርቷን ነገር ዲፕሎማ ላይ አልተወችውም። “ዲፕሎማ የትም ይገኛል። በዚህ ስራ ይዣለሁ ብለሽ እንዳትዘናጊ” የሚለው የአባቷ ምክር ለተሻለ ነገር እንድትተጋ አድርጓታል። በትዳር ውስጥ ሆና ልጅ እያሳደገች ጭምር 2005 ዓ.ም ላይ በዲግሪ ተመርቃለች።

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የሰጣትን የትምህርት ዕድል ተጠቅማ የማስተርስ ዲግሪዋን ይዛለች። አሁን ደግሞ በተለይም የጀመረችውን የአመራርነት መንገድ ለማጠናከር እንዲረዳት በማሰብ በሊደርሺፕ ማኔጅመንት በግሏ ለሌላ ማስተርስ ዲግሪ በመማር ላይ ትገኛለች። ታታሪዋ ነርስ በትዳርም ስኬታማ ናት። ለስኬቷ ሁሉ አጋዥ ባል አላት። በትዳር ቆይታዋም ሁለት ልጆችን አፍርታለች።