የጋሞ ዞን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የምርጫ ካርድ የመጣል ሂደት መጠናቀቁን ተከትሎ መግለጫ ሰጡ
ምክር ቤቱ የቅድመ-ምርጫ፣ የምርጫ ወቅትና የድህረ-ምርጫ ሥራዎችን በዝርዝር ከገመገመ በኋላ ነው ወቅታዊ አቋሙን ይፋ ያደረገው።
የምክር ቤቱ ሰብሳቢ መምህር ቴዎድሮስ ፋንታዬ እና ምክትል ሰብሳቢው አቶ ተመስገን እዩኤል የጋራ አቋማቸውን በገለጹበት ወቅት፤ ማህበረሰቡ በነቂስ ወጥቶ፣ በሰላም ካርዱን ጥሎ ያለምንም የጸጥታ ችግር ወደ ቤቱ መመለሱን አንስተዋል።
በሂደቱ ላይ የተስተዋሉ ማናቸውም ቅሬታዎች የምርጫው ህግ በሚፈቅደው መሠረት ብቻ ምላሽ ማግኘት አለባቸውም ተብሏል።
ምክር ቤቱ ይፋዊ የምርጫ ውጤት በይፋ እስኪገለጽ ድረስ መላው ህብረተሰብ የተለመደውን የዲሞክራሲ ባህል በማሳየት በትዕግስት መጠበቅ ይኖርበታል ብለዋል።
የጋራ ምክር ቤቱ ፈታኙን የአየር ንብረት ተቋቁሞ፣ የዜግነት ግዴታውን በሰላማዊ መንገድ ለተወጣውና ለሂደቱ ስኬት ዋነኛ ባለቤት ለሆነው መላው ማህበረሰብ የላቀ ምስጋና አቅርቧል።
ዘጋቢ : አማሮ አርሳባ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
የጋሞ ዞን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የምርጫ ካርድ የመጣል ሂደት መጠናቀቁን ተከትሎ መግለጫ ሰጡ

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው