ሊቨርፑል አሰልጣኝ አርኔ ስሎትን አሰናበተ
የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዋና አሰልጣኙን አርኔ ስሎት ከሀላፊነት ማሰናበቱን አሳውቋል።
ሆላንዳዊው አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ሊቨርፑልን በተረከቡበት ባለፈው የውድድር ዘመን ክለቡን ለ20ኛ ጊዜ የሊጉ ሻምፒዮን እንዲሆን ቢያስችሉም ዘንድሮ ባስመዘገቡት ደካማ ውጤት ከሀላፊነታቸው ተነስተዋል።
ሊቨርፑል በዘንድሮው የውድድር በሁሉም ውድድሮች በ19 ጨዋታዎች ተሸንፎ በሊጉ 5ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወቃል።
አሰልጣኝ ዩርገን ክሎፕን ተክተው እንግሊዝ የደረሱት የ47 ዓመቱ አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ሁለት ዓመታትን ብቻ በሊቨርፑል ቆይተው ነው የተሰናበቱት።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ አስፈረመ
ማንቸስተር ዩናይትድ አንድሬ ሳንቶስን አስፈረመ
የ2018 የCBE የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በማሸነፍ ሁለት ዋንጫ ላነሳው የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ክልሉ ያዘጋጀውን የዕውቅናና የሽልማት ፕሮግራም ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 06/2018 ከቀኑ 12፡00 ጀምሮ በሀዋሳ ሀይሌ ሪዞርት ይካሄዳል።