ማንቸስተር ዩናይትድ የአታላንታውን አማካይ ኤደርሰንን ለማስፈረም ተቃረበ

ማንቸስተር ዩናይትድ የአታላንታውን አማካይ ኤደርሰንን ለማስፈረም ተቃረበ

ማንቸስተር ዩናይትድ የአታላንታውን ብራዚላዊ አማካይ ኤደርሰንን የመጀመሪያ የክረምቱ ዝውውር ፈራሚ ለማድረግ መቃረቡ ተገልጿል።

ዘገባዎች እንደሚያመላክቱት ለ26 ዓመቱ ተጫዋች የመጀመሪያ ክፍያ 35 ሚሊየን ፓውንድ እና ተጨማሪ 3 ሚሊየን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ ስምምነት ላይ ሊደረስ ተቃርቧል።


የካሴሚሮን መልቀቅ እና የማኑኤል ኡጋርቴ የወደፊት እጣ ፈንታ አለመወሰን ተከትሎ ዩናይትድ በዚህ ክረምት አማካይ ክፍሉን ማጠናከርን ቀዳሚ አጀንዳው አድርጎታል።

በዚያ ቦታ ላይ ሁለት ወይም ምናልባትም ሦስት ተጫዋቾችን ለማስፈረም በዝውውር ገበያው ይንቀሳቀሳል ተብሎ ይጠበቃል።

የኤደርሰን ዝውውር በዚህ ሳምንት መጨረሻ ሊጠናቀቅ እንደሚችልም ተዘግቧል።

የአታላንታው አሰልጣኝ ራፋኤሌ ፓላዲኖ ባለፈው ሳምንት ከፊዮረንቲና ጋር ባደረጉት ጨዋታ ኤደርሰን ለምን ተጠባባቂ ወንደበር ላይ እንዳስቀመጡት ተጠይቀው “አንድ ትልቅ ክለብ እየተከታተለው በመሆኑ ነው” በማለት አረጋግጠው ነበር።

ኤደርሰን ወደ አትሌቲኮ ማድሪድ ያመራል ተብሎ ቢጠበቅም ነገር ግን የስፔኑ ክለብ ትኩረቱን ወደ ዎልቭሱ ጆአዎ ጎሜዝ ማዞሩ ካሴሚሮን ለመተካት ለሚፈልገው ማንቸስተር ዩናይትድ ዕድሉን ከፍቶለታል።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ