ማንቸስተር ሲቲ አንደርሰንን ለማስፈር በሚደረገው ፉክክር ከማንቸስተር ዩናይትድ ቀዳሚነቱን ያዘ

ማንቸስተር ሲቲ አንደርሰንን ለማስፈር በሚደረገው ፉክክር ከማንቸስተር ዩናይትድ ቀዳሚነቱን ያዘ

የኖቲንግሃም ፎረስት አማካይ ኤሊዮት አንደርሰን ወደ ተቀናቃኙ ማንቸስተር ዩናይትድ ከማምራት ይልቅ ወደ ኢቲሃድ ስታዲየም የመዘዋወር ዝንባሌ እያሳየ በመሆኑ ማንቸስተር ሲቲ ተጫዋቹን ለማስፈረም በሚደረገው ፉክክር ቀዳሚነቱን ይዟል።



የ23 ዓመቱ አንደርሰን በዚህ ክረምት ከሲቲ ግራውንድ ይወጣል የሚለው ግምት እየጨመረ መጥቷል።

 ተጫዋቹን ለማስፈረም በሚደረገው ፉክክር ማንቸስተር ዩናይትድ ከተገቢው በላይ ዋጋ ለመክፈል ወይም በተራዘመ ድርድር ውስጥ ለመግባት ፍላጎት እንደሌለው ተዘግቧል።

በፎረስት እና በሲቲ መካከል እስካሁን የተደረሰ ስምምነት የለም።

 የዝውውር ዋጋው ለአንድ ብሪታንያዊ ተጫዋች የተከፈለ የምንጊዜውም ከፍተኛ ክብረወሰን ሊሆንና አርሰናል በ2023 ለዴክላን ራይስ ለዌስትሃም ከከፈለው £105 ሚሊዮን ሊበልጥ እንደሚችል ቢቢሲ አስነብቧል።

ተጫዋቹ ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጋር በመጪው የዓለም ዋንጫ ላይ የሚያሳየው ጥሩ ብቃት ደግሞ ክለቡን የተሻለ የድርድር አቅም ላይ ያኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

ባለፈው ክረምት ከእንግሊዝ ከ21 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጋር የ2025 የአውሮፓ ሻምፒዮናን ያሸነፈው አንደርሰን፣ በ2024 ከኒውካስል ፎረስትን የተቀላቀለው በ£35 ሚሊዮን ሲሆን፣ ለክለቡ 92 ጨዋታዎችን አድርጎ ስድስት ጎሎችን አስቆጥሯል።

ባሳለፍነው እሁድ ከቦርንማውዝ ጋር የተደረገው ጨዋታ በዚህ የውድድር ዘመን 50ኛ ጨዋታው የነበረ ሲሆን፣ በሁለተኛው አጋማሽ ሲቀየር በስታዲየሙ የነበሩ ደጋፊዎች ቆመው በጭብጨባ ሸኝተውታል።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ