ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ መድህንን በማሸነፍ ወደ ፍፃሜ አለፈ
በኢትዮጵያ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ሲዳማ ቡና የወቅቱን የሊጉ ሻምፒዮን ኢትዮጵያ መድህንን በመለያ ምት በማሸነፍ ወደ ፍፃሜ አልፏል።
በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም የተካሄደው የሁለቱ ክለቦች መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 2 አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
በጨዋታ ለሲዳማ ቡና መስፍን ታፈሰ እና ያሬድ ባየህ (በፍፁም ቅጣት) ሲያስቆጥሩ ለኢትዮጵያ መድህን አማኑኤል ኤርቦ አስቆጥሯል።
አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠው የመለያ ፍፁም ቅጣት ምት ሲዳማ ቡና 4ለ3 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት ለፍፃሜ ደርሷል።
በፍፃሜው የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ጋር የሚጫወት ይሆናል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ አስፈረመ
ማንቸስተር ዩናይትድ አንድሬ ሳንቶስን አስፈረመ
የ2018 የCBE የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በማሸነፍ ሁለት ዋንጫ ላነሳው የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ክልሉ ያዘጋጀውን የዕውቅናና የሽልማት ፕሮግራም ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 06/2018 ከቀኑ 12፡00 ጀምሮ በሀዋሳ ሀይሌ ሪዞርት ይካሄዳል።