በጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ እና በላሃ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ የማጠቃለያ ሕዝባዊ የምርጫ ቅስቀሳ ፕሮግራም ተካሄደ
ሀገር ለማሸገር የተያዘውን ዉጥን ዕውን ለማድረግ እንደሚሰራም ተገልጿ።
በመርሐ ግብሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ማሩፋ መኩሪያ የድጋፍ ሰልፉ ዋና ዓላማ ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ያስመዘገባቸውን ድሎችን ለማስቀጠል እና ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገር የተቀመጠውን ግብ ዕውን ለማድረግ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።
ሕዝቡ በድጋፍ ሰልፉ ያሳየውን ተሳትፎ እና አንድነት በድምጽ መስጫ ዕለትም እንዲደግም ጥሪ አቅርበዋል።
የጎፋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የስራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ ምናሴ ኤልያስ ብልፅግና ፓርቲ ከህብረተሰቡ የሚነሱ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች በየደረጃቸው እየተመለሱ መምጣታቸውን ተናግረው በጅምር ያሉ የህዝብ ጥያቄን ለመጨረስ ብልፅግና ፓርቲን በመምረጥ የተደመረውን ልማት ማሰቀጠል እንዲችሉ አሳሰበዋል።
የመሎ ምርጫ ክልል የብልጽግና ፓርቲ የፌዴራል ተወካይ ኢንጂነር ካሳሁን ሰለሞን ብልፅግና ፓርቲ የማህበረሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በየጊዜው እየለየ በመፍታት የልማትና የዕድገት ጉዞ ቀጣይነት እንዲኖረው በምርጫ ካርድ እንዲያረጋግጡ ጥሪ አቅርበዋል።
የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት በማስገንዘብ ለመጪው የልማት ጉዞ ብልፅግና ፓርቲን ይምረጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በተካሄደው የይምረጡኝ ምርጫ ቅስቀሳ ማጠቃለያ መርሐ ግብር ላይ የፌዴራል፣ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም አባላትና ደጋፊዎች የድጋፍ ሰልፉን በባህላዊ ትዕይንት አቅርበዋል።
ዘጋቢ – ስንታየሁ ሙላቱ – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው