ታናሹ የፕሪሚዬር ሊጉ ሻምፒዮን!
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አዳዲስ ታሪኮችን መውለድ አይታክተውም። ዛሬ የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከ22 ዓመታት ረጅ በኋላ የፕሪሚየር ሊጉን ዘውድ ሲደፋ፣ ከአዲሱ ታሪክ ጀርባ አንድ እጅግ አስገራሚ ታዳጊ ስም በጉልህ ተጽፏል – ማክስ ዶውማን።
የማንችስተር ሲቲ በቦርንማውዝ መሸነፍ ለአርሰናል የሻምፒዮንነት አክሊልን ሲያቀዳጅ፣ ዶውማን ሌላ ትልቅ የታሪክ ባለቤት ሆኗል።
የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ በማንሳት በዕድሜ ትንሹ ተጫዋች የመሆን ክብርን ተቀናጅቷል።
በመጪው እሁድ፣ በሊጉ የመጨረሻ ቀን ላይ እድሜው 16 ዓመት ከ144 ቀን ብቻ ቢሆንም፣ ለአርሰናል ሻምፒዮናዎች ከሚታደሉት 40 የወርቅ ሜዳሊያዎች አንዱን በአንገቱ ያጠልቃል።
በሊጉ ህግ መሰረት አንድ ተጫዋች የሻምፒዮንነት ሜዳሊያ ለማግኘት ቢያንስ 5 የሊግ ጨዋታዎችን ማድረግ ይኖርበታል። ዶውማን ዘንድሮ በ5 ጨዋታዎች ላይ ተቀይሮ በመግባት ይህንን መስፈርት አሟልቷል።
ዳውማን ክብረወሰኑን የወሰደው ከማን ከማንችስተር ሲቲው የፊት መስመር ተጫዋች ፊል ፎደን ነው።
ይህ ብላቴና ዘንድሮ የሰራቸው ተአምራት ዝም ብለው የመጡ አይደሉም። የክለቡንና የሊጉን ታሪክ በአንድ የውድድር ዓመት ውስጥ እንዴት እንዳፈራረሰው ስንመለከት በ15 ዓመት ከ235 ቀኑ ተሰልፎ በመጫወት በፕሪሚየር ሊጉ ታሪክ ታናሹ ተጫዋች ሆነ።
በ15 ዓመት ከ308 ቀኑ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሰልፎ በመጫወት በውድድሩ ታሪክ በዕድሜ ትንሹ ተጫዋች መሆን ቻለ።
በኤምሬትስ ስታዲየም በኤቨርተን ላይ ያስቆጠራት ያች አስደናቂ ጎል በ16 ዓመት ከ73 ቀኑ የሊጉ ታናሽ ጎል አስቆጣሪ አደረገችው።
አርሰናሎች የ22 ዓመታት የዋንጫ ድርቃቸውን ሲመቱ፣ የወደፊት ብሩህ ተስፋቸውንም ጭምር ነው ያገኙት።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ አስፈረመ
ማንቸስተር ዩናይትድ አንድሬ ሳንቶስን አስፈረመ
የ2018 የCBE የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በማሸነፍ ሁለት ዋንጫ ላነሳው የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ክልሉ ያዘጋጀውን የዕውቅናና የሽልማት ፕሮግራም ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 06/2018 ከቀኑ 12፡00 ጀምሮ በሀዋሳ ሀይሌ ሪዞርት ይካሄዳል።