መድፈኞቹ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ሊጽፉ አንድ ሐሙስ ቀርቷቸዋል!
የ22 ዓመታት የዋንጫ ናፍቆት፣ የትውልድ ቅብብሎሽ ስቃይ እና የደጋፊዎች የልብ ትርታ ዛሬ ምሽት ኤምሬትስ ስታዲየም ላይ ያርፋል።
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ37ኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሃ-ግብር፣ ሰሜን ለንደንን ቀይ ለማልበስ የተቃረበው አርሰናል ከወራጅ ቀጠናው ስንብቱን ካረጋገጠው በርንሌይ ጋር ይጋጠማል።
ለሊጉ ክብርና ክብር ብቻ የሚጫወተው አርሰናል ዛሬ የሚያገኘው 3 ነጥብ፣ ወደ ኤምሬትስ ለሚመጣው የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ትልቁን በር የሚከፍት ይሆናል።
አርሰናል ከበርንሌይ ጋር ባደረጋቸው ያለፉት 19 የሊግ ጨዋታዎች ላይ የነበረው የበላይነት ፍጹም አስደናቂ ነው።
አርሰናል 14 ጨዋታዎችን በድል ሲያጠናቅቅ 4 ጨዋታዎችን ደግሞ አቻ ተለያይቷል።
የሰሜንለንደኑክለብበበርንሌይየተሸነፈው በ1 ጨዋታ ብቻ ነው።
ይህ ታሪካዊ የበላይነት ለመድፈኞቹ የስነ-ልቦና ስንቅ ቢሆንም፣ የእግር ኳስ ውበት ግን 90 ደቂቃ ሜዳ ላይ በሚታየው ትግል ብቻ መወሰኑ ነው።
ምንም እንኳ በጊዜያዊ አሰልጣኙ ማይክል ጃክሰን የሚመሩት ክላሬትሶቹ ቀድመው መውረዳቸው ቢረጋገጥም፣ ባለፈው ሳምንት ከአስቶን ቪላ ጋር 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት መለያየታቸው ዛሬም በቀላሉ እጃቸውን እንደማይሰጡ ማሳያ ነው።
በተለይም የቀድሞው የማንችስተር ሲቲ ተከላካይና አሁን የበርንሌይ የጀርባ አጥንት የሆነው ካይልዎከር “በኤምሬትስጥሩውጤትአስመዝግበንክብራችንንአስጠብቀንመውጣትእንፈልጋለን“ ሲል የሰጠው አስተያየት ጨዋታው ለአርሰናል የአልጋ በአልጋ እንደማይሆን ይጠቁማል።
አርሰናል ዛሬ ምሽት 4:00 ላይ በርንሌይን ካሸነፈ በኋላ አይኑን ወደ ነገው ጨዋታ ያዞራል።
ነገ ማንችስተር ሲቲ በቦርንማውዝ ሜዳ ነጥብ የሚጥል ከሆነ፣ የአርሰናል የዘንድሮው የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት በይፋ ይረጋገጣል!
በምሽቱጨዋታበአርሰናልበኩል
ቤን ዋይት፣ ዩሪየን ቲምበር እና ሚኬል ሜሪኖ በጉዳት ምክንያት ከጨዋታው ውጪ የሆኑ ተጫዋቾች ሲሆኑ
ተከላካዩ ሪካርዶ ካላፊዮሪ መሰለፉ አጠራጣሪ መሆኑ ተዘግቧል።
በበርንሌይበኩል ጆርዳን ቤየር፣ ኮኖር ሮበርትስ እና ጆሽ ካለን ከጨዋታውውጪየሆኑ ተጫዋቾች ሲሆኑ የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ አማካይ ሀኒባል መጅብሪ መሰለፉ አጠራጣሪ ነው።
ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ
መድፈኞቹ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ሊጽፉ አንድ ሐሙስ ቀርቷቸዋል!

More Stories
“የቤት ስራችንን ለመጨረስ ተቃርበናል” — ሚኬል አርቴታ
«ራይስ አርሰናልን መምረጡ ያበሳጨኛል» ብሩኖ ፈርናንዴዝ
“የወደፊት ቆይታዬ በቅርቡ ይወሰናል” ማይክል ካሪክ