“የወደፊት ቆይታዬ በቅርቡ ይወሰናል” ማይክል ካሪክ
በታላቁ ኦልድትራፎርድ ስታዲየም የለውጥ ነፋስ እየነፈሰ ነው። የሰር ጂም ራትክሊፍ አዲስ አስተዳደር የማንችስተር ዩናይትድን የክብር ዘመን ለመመለስ ትልልቅ ውሳኔዎችን እያሳለፈ በሚገኝበት በዚህ ወሳኝ ወቅት፣ የሁሉም አይኖች በአንድ ሰው ላይ አርፈዋል— በክለቡ የቀድሞው ታሪክ ሰሪ እና የአሁኑ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ።
ካሪክ ክለቡን በጊዜያዊነት ከተረከቡበት ጊዜ ጀምሮ ያሳዩትው መረጋጋት እና የታክቲክ ብስለት፣ አዲሱ የክለቡ የበላይ አካል ለቋሚ አሰልጣኝነት ቀዳሚ እጩ አድርጎ እንዲመርጣቸዉ ትልቅ ግፊት ፈጥሯል።
ማይክል ካሪክ ማንቸስተር ዩናይትድ በፈታኝ ወቅት ላይ ሳለ ቡድኑን ተረክበዉ ያሳዩት አስደናቂ ስኬት የሚካድ አይደለም። በኃላፊነት በቆየባቸው 15 ጨዋታዎች ብቻ ቡድኑን ወደ ሻምፒዮንስ ሊግ መመለስ ችሏል።
ከዚህም በላይ እንደ ማንቸስተር ሲቲ፣ ሊቨርፑል፣ አርሰናል እና ቼልሲ ያሉ የሊጉን ግዙፍ ክለቦች በታክቲክ ብልጫ ማሸነፉ የክለቡን የበላይ አካላት አምነት እንዲያተርፍ አድርጎታል።
የክለቡ የሊግ የመጨረሻ የሜዳዉ ጨዋታ ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር ከመደረጉ በፊት ካሪክ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ስለ ውሉ ሁኔታ ተጠይቀዉ “የእኔ የወደፊት እጣ ፈንታ በጣም በቅርቡ ይወሰናል። ከዚህ በኋላ የሚመጣው ነገር ምን እንደሆነ ለማወቅ በጣም ተቃርበናል” ሲሉ ተናግሯል፡፡
የክለቡ የስፖርት ዳይሬክተር ጄሰን ዊልኮክስ እና ዋና ስራ አስፈፃሚው ኦማር ቤራዳ ካሪክ ቡድኑን በቋሚነት እንዲመራ ሙሉ እምነት ጥለውባቸዋል።
በአሁኑ ሰዓት ከክለቡ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ንግግር እየተደረገ ሲሆን፣ ስምምነቱ የውድድር ዘመኑ ከመጠናቀቁ በፊት ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
ማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ በክለቡ በቋሚነት እንዲቀጥሉ በይፋ ውል እንደቀረበላቸዉ ዘ አትሌቲክ በዛሬዉ ዕለት አስነብቧል።
ማይክል ካሪክ ለአንድ ተጨማሪ አመት የመቆየት አማራጭ ያካተተ የሁለት አመት ውል እንደቀረበላቸው ተገልጿል።
ዘጋቢ ፡ ሙሉቀን ባሳ
“የወደፊት ቆይታዬ በቅርቡ ይወሰናል” ማይክል ካሪክ

More Stories
“ዳኛው ትክክለኛ ውሳኔ በመወሰኑ ደስተኛ ነኝ” ሚኬል አርቴታ
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ዕጩዎች ይፋ ሆኑ
የአርሰናል የድል ጉዞ እና የዌስትሃም ቁጭት!