የአርሰናል የኋላ ደጀን ቤን ዋይት የውድድር ዓመቱ በጉዳት ተጠናቀቀ
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በፕሪምየር ሊጉ የዋንጫ ፉክክር እና በሻምፒዮንስ ሊግ ታሪክ ለመስራት በሚያደርገው ጉዞ ላይ መጥፎ ዜና ተሰምቷል።
የክለቡ ሁለገብ ተከላካይ ቤን ዋይት በደረሰበት ከባድ የጉልበት ጉዳት ምክንያት ቀሪ የውድድር ዘመን ጨዋታዎች እንደሚያመልጡት ታውቋል።
ቤን ዋይት ጉዳቱ የገጠመው አርሰናል ዌስትሀም ዩናይትድን በረታበት የለንደን ደርቢ ጨዋታ ላይ እንደነበር ይታወሳል።
ጉዳቱ መጀመሪያ ላይ ቀላል መስሎ ቢታይም፣ የተደረገለት ጥልቅ የህክምና ምርመራ ግን ተጫዋቹ ለረጅም ጊዜ ከሜዳ እንደሚርቅ ተረጋግጧል።
ይህ ዜና ለሚኬል አርቴታ ትልቅ ራስ ምታት ሆኗል።ቤን ዋይት በሜዳ ላይ ባለው ብስለት እና በማጥቃትም ሆነ በመከላከል ረገድ የሚሰጠው ሚዛን ለአርሰናል በቀላሉ የማይተካ ነው።
ቤን ዋይት በጉዳት ምክንያት የአርሰናል የመጨረሻዎቹ ወሳኝ የሊግ ጨዋታዎች እና ከፒኤስጂ ጋር የሚደረገው የሻምፒዮንስ ሊጉ የፍፃሜ ጨዋታ የሚያመልጠው ይሆናል።
ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ
የአርሰናል የኋላ ደጀን ቤን ዋይት የውድድር ዓመቱ በጉዳት ተጠናቀቀ

More Stories
ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ አስፈረመ
ማንቸስተር ዩናይትድ አንድሬ ሳንቶስን አስፈረመ
የ2018 የCBE የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በማሸነፍ ሁለት ዋንጫ ላነሳው የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ክልሉ ያዘጋጀውን የዕውቅናና የሽልማት ፕሮግራም ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 06/2018 ከቀኑ 12፡00 ጀምሮ በሀዋሳ ሀይሌ ሪዞርት ይካሄዳል።