ዣቪ አሎንሶ ለቼልሲው የአሰልጣኝነት ቦታ ዋነኛው እጩ ሆኖ ብቅ ብሏል
ቼልሲ የክለቡን ቀጣይ ቋሚ ዋና አሰልጣኝ ለመሾም በሚያደርገው ጉዞ፣ እጩ ከሆኑ ግለሰቦች ጋር ንግግር ማድረግ ጀምሯል።
ባለፈው ወር ከኃላፊነታቸው ከተነሱት ሊያም ሮዜንየር ለመተካት በዝርዝሩ ውስጥ ስማቸው ከሰፈሩት መካከል አንዶኒ ኢራኦላ፣ ዣቪ አሎንሶ እና ማርኮ ሲልቫ እንደሚገኙበት ታውቋል።
ከእነዚህም በተጨማሪ የክሪስታል ፓላሱ ዋና አሰልጣኝ ኦሊቨር ግላስነር በቼልሲ የዕጩዎች ዝርዝር ውስጥ መካተቱ ተነግሯል።
ክለቡ አዲሱን ዋና አሰልጣኝ በሐምሌ ወር መጀመሪያ ላይ ከሚጀመረው የቅድመ-ውድድር ዝግጅት ልምምድ ቀደም ብሎ ለመሾም ተስፋ አድርጓል።
የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ፣ በውጤት ማጣት ሲናወጥ ከቆየ በኋላ አሁን የአዲሱን መሪ ፍለጋ ጉዞውን አጧጡፏል።
ስካይ ስፖርትስ እንደዘገበው ከሆነ፣ በክለቡ የስፖርት ዳይሬክተሮች ጠረጴዛ ላይ በግንባር ቀደምትነት የተቀመጠው ስም አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ ነው።
አሎንሶ በሌቨርኩሰን የሰራው ተአምር ብቻ ሳይሆን፣ በእግር ኳስ ተጫዋችነቱ ያሳለፈው ድንቅ ስብዕና የቼልሲን ባለቤቶች ቀልብ ስቧል።
ይሁን እንጂ የዚህ ታሪክ አስገራሚው ገፅታ አሎንሶ በሪያል ማድሪድ ቤት በቂ ጊዜ ሳይሰጠው ‘ያልተጠናቀቀ የቤት ስራ’ ይዞ መውጣቱ ነው።
አሁን ግን ያ ያልተጠናቀቀ ታሪክ በለንደን ምድር ላይ ዳግም ሊቀጥል እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል።
ቼልሲዎች ‘ልምድና ስኬት’ አጣምሮ የያዘ መሪ ይፈልጋሉ። አሎንሶ ደግሞ የኳስ ቁጥጥርን ከጥቃቅን ታክቲካዊ ትንታኔዎች ጋር አቀናጅቶ በመተግበር ረገድ በዓለም ላይ ካሉ ወጣት አሰልጣኞች በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል።
ክለቡ በአሁኑ ሰዓት ትኩረቱን በኤፍ ኤ ካፕ ፍፃሜ ላይ ቢያደርግም፣ በስተጀርባ ግን ከአሎንሶ ወኪሎች ጋር የሚደረገው ድርድር ‘በከፍተኛ ጥንቃቄ’ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተዘግቧል።
ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ
ዣቪ አሎንሶ ለቼልሲው የአሰልጣኝነት ቦታ ዋነኛው እጩ ሆኖ ብቅ ብሏል

More Stories
ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ አስፈረመ
ማንቸስተር ዩናይትድ አንድሬ ሳንቶስን አስፈረመ
የ2018 የCBE የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በማሸነፍ ሁለት ዋንጫ ላነሳው የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ክልሉ ያዘጋጀውን የዕውቅናና የሽልማት ፕሮግራም ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 06/2018 ከቀኑ 12፡00 ጀምሮ በሀዋሳ ሀይሌ ሪዞርት ይካሄዳል።