የታርጫ ህዝብ ትራንስፖርት መናኸሪያ በርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

የታርጫ ህዝብ ትራንስፖርት መናኸሪያ በርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 23/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በዳውሮ ዞን የታርጫ ከተማ ህዝብ ትራንስፖርት መናኸሪያ በርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡

በዳውሮ ዞን የታርጫ መነኻሪያ ግንባታ በቀድሞው ክልል ተጀምሮ ሳይጠናቀቅ የቆየ ቢሆንም የታርጫ ህዝብ ትራንስፖርት መናኸሪያ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በአዲስ መልክ በተደራጀ ማግስት የግንባታ ሂደት እንዲቀጥል ተደርጎ የተጠናቀቀ መሆኑ ተገልጿል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ባለቤትነትና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ኮንስትራክሽን ባለስልጣን አማካሪነት የተገነባ ፕሮጀክት መሆኑንም ተጠቁሟል።

መናኸሪያው የተሳፋሪ ሸዶችን ጨምሮ ዘመናዊ ቢሮዎች፣ ካፍቴሪያ፣ የመረጃ መስጫና የትኬት መቁረጫ ክፍሎች ያሉት ሲሆን፥ የግንባታ ጠቅላላ ወጪ 99.15 ሚሊዮን ብር መሆኑ ተመልክቷል።

በምረቃው ፕሮግራሙ ላይ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የክልሉ የስራ ኃላፊዎች፣ የዳውሮ ዞን አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የታርጫ መነኻሪያ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡

ዘጋቢ፡ አዲስዓለም ታዬ – ከዋካ ጣቢያችን