በ25 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የማሪ ቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል በርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) መርቀው የከፈቱት የግብይት ማዕከሉ በ25 ሚሊየን ብር ወጪ ተገንብቶ የተጠናቀቀ እንደሆነ ተገልጿል።
ግንባታው በ11 ወራት ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቀ መሆኑ ተጠቁሟል።
በዳውሮ ዞን የማሪ አካባቢ ከፍተኛ የቁም እንስሳት ግብይት የሚፈፀምበት በመሆኑ የግብይት ማዕከሉ ግንባታ የግብይት ሂደትን ከማቀላጠፍ በተጨማሪ ለገቢ አሰባሰብ ሂደት ቅልጥፍናን ይፈጥራል ተብሏል።
ከ10 ሺህ 2 መቶ በላይ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው የግብይት ማዕከሉ የእንስሳት መገበያያ፣ ከማዕከሉ ተገዝተው ወደሌላ ቦታ ለሚወሰዱ እንስሳት ወደ መኪና መጫኛ ቦታ፣ የታመሙ እንስሳት ተለይተው የሚቆዩበት ህክምና ቦታን አካቶ የተሠራ ነው።
ዘጋቢ፡ ዮሐንስ መካሻ – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
መሬት ውስን የተፈጥሮ ሀብት በመሆኑ በአግባቡ በመምራትና ከብክነት በመጠበቅ ቀጣይነት ያለዉን ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ
መስቀል የድህነት ምልክት መሆኑን የካፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮና ምዕራብ ኦሞ አህጉረ-ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ህዝቅኤል ተናገሩ