7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ፍትሃዊ እንዲሆን ሰፊ ተግባራት መከናወናቸውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ

7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ፍትሃዊ እንዲሆን ሰፊ ተግባራት መከናወናቸውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በቴፒ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመርሃ-ግብሩ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን እንደገለፁት፤ በዓመቱ ምርጫ ለማካሄድ አንድ ወር በቀረው ጊዜ ውስጥ የዘጠኝ ወር አፈፃፀም መገምገሙ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ ግምገማ በማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ያለውን ግንኙነት ማሻሻልና የዲሞክራሲ ምህዳሩን ማስፋት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱንም አንስተዋል።

7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ፍትሃዊ እንዲሆን የምርጫ ኮሚቴዎችን እስከ ቀበሌ በማደራጀት ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ሰፊ ተግባራት ተከናውነዋል ያሉት ኃላፊዉ፤ ምርጫው እስከሚጠናቀቅም በልዩ ትኩረት ይሰራል ብለዋል።

ዜጎች የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ በስፋት መሰራቱ፣ የጋራ ምክር ቤት በማዘጋጀት የጋራ ምክክር ማድረጉ፣ የኮማንድ ፖስት ስራዎችና በርካታ ስልጠናዎችን መስጠት መቻሉ ውጤት ለማስመዝገብ የተከናወኑና በጥንካሬ የተሰሩ ሥራዎች ናቸው ብለዋል።

በዚህም ምርጫው ሰላማዊ፣ ፍትሐዊ፣ ተዓማኒና ግልፀኝነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡

ዘጋቢ: ምንታምር አስፋው – ከማሻ ጣቢያችን