ባለፉት ዘጠኝ ወራት በፓርቲው መሪነት በልማት፣ በመልካም አስተዳደር እና በፖለቲካው ዘርፍ አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል – አቶ ፍቅሬ አማን
ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 19/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት በፓርቲው መሪነት በልማት፣ በመልካም አስተዳደር እና በፖለቲካው ዘርፍ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልፅግና ፓርቲ የዘጠኝ ወራት የፓርቲ ተግባር አፈፃፀም ግምገማ በቴፒ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
መድረኩን በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት የከፈቱት የሸካ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ፤ ብልፅግና ፓርቲ ዕቅድን ወደ ተግባር እየለወጠ የመጣ ፓርቲ መሆኑን ተናግረው ክልሉ ከተቋቋመ ወዲህ ኢ-ፍትሃዊ የሆኑ አሰራሮችን እየቀረፈ መጥቷል ብለዋል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን እንደተናገሩት፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በፓርቲው መሪነት በልማት፣ በመልካም አስተዳደር እና በፖለቲካው ዘርፍ አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል።
በተለይም የፓርቲ ኢኒሼቲቮች በሆኑ የገጠር ኮሪደር፣ የሌማት ትሩፋትና መሠረተ ልማት ግንባታዎችን በመተግበር ለውጥ እየተመዘገበ መሆኑን ገልፀው በፍጥነት ከመጓዝ አንፃር አሁን ብዙ ስራዎች ይጠበቃሉ ብለዋል።
የፓርቲ አደረጃጀቶችን በማጠናከርና ኮማንድ ፖስት እስከታችኛው መዋቅር በመዘርጋት የመረጃ ልውውጡን ማሳለጥና የአባላት አቅም ግንባታ ለማሳደግ ስልጠናዎች መስጠት መቻሉንም ተናግረዋል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቶች እንቅስቃሴ በጥሩ ደረጃ ላይ ያለ መሆኑን ጠቁመው፤ ከፖለቲካ ፓርቲ ጋር ያለውን ግንኙነት በማሳደግ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
ለተገልጋዩ፣ ለአባላቱና ለህብረተሰቡ ቀልጣፋና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት በተለያዩ መዋቅሮች የፓርቲው ጽሕፈት ቤት ግንባታዎች እየተካሄዱ እንደሚገኙ ገልፀዋል።
ሀገሪቱ በ2030 ሙሉ በሙሉ የዲጂታል አገልግሎት ለመስጠት በያዘችው ውጥን አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል በመቀየር ህብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ እየተሰራ ነው ብለዋል።
የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን በአምስት ከተሞች ለመስጠት ታቅዶ ግንባታዎች እየተካሄዱ መሆናቸውን ገልፀው በዚህም የመልካም አስተዳደር ችግሮች ይቀረፋሉ ብለዋል።
በውስጥም በውጭም የሚካሄዱ ሴራዎችን በማክሸፍ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የለውጥ ጉዞ እውን በማድረግ ወደ ተምሳሌት ሀገር ማሸጋገር ይገባል ብለዋል።
ዘጋቢ: በዛብህ ታደሰ – ከማሻ ጣቢያችን

More Stories
7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ፍትሃዊ እንዲሆን ሰፊ ተግባራት መከናወናቸውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ
በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በመማር ማስተማር ዘርፍ እየተመዘገቡ የሚገኙ ለወጦች ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ
ባለፉት ዘጠኝ ወራት 5.5 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች በተለያዩ ዘርፎች ወደስራ መግባታቸውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ