በዳዉሮ ዞን እየተሠሩ የሚገኙ የልማት ሥራዎች ለህዝቡ የመልማት ጥያቄ ምላሽ እያስገኙ መሆናቸዉ ትኩረት ሊደረግባቸው እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ

በዳዉሮ ዞን እየተሠሩ የሚገኙ የልማት ሥራዎች ለህዝቡ የመልማት ጥያቄ ምላሽ እያስገኙ መሆናቸዉ ትኩረት ሊደረግባቸው እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ

በዞኑ የመሰረተ ልማት፣ መልካም አስተዳደር እና የዜጎችን ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ዉይይት ተካሂዷል።

ከዚህ ቀደም በዞኑ የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ በርካታ ጥያቄዎችን እያስነሳ የሚገኘው የሕዝቡ የመልማት ፍላጎት በለውጡ መንግሥት ምላሽ እያገኘ መምጣቱን የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም በዞኑ የሚነሳዉን የመልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በአግባቡ ምላሽ እንዲያገኙ በትኩረት መሰራት የሚገባም ገልጸዋል፡፡

አመራሩ ስትራቴጂካዊ በመሆን ለችግሮች መፍትሄ በመስጠት የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

በዚሁ አግባብ በመርህ ላይ የተመሰረተ ተቋም የግንባታ ሂደትን በቴክኖሎጂ በማዘመን የአገልግሎት አሰጣጥ በወጥነት እንዲመራ ለማስቻል መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ በበኩላቸው፤ የአመራሩን አቅም በመገንባትና ህዝባዊ መሰረት ለማስያዝ የዳበረ ክህሎት ለማስፋፋት እንደዚህ ዓይነት ዉይይቶች አይተኬ ሚና እንዳለቸው ገልፀዋል።

የዉይይት መድረኩ የአመራርን አቅም ከማዳበር ባለፈ በዚሁ መድረክ የተነሱ ጉዳዮች፣ ምላሽ እንዲያገኙ ለማስቻል አበክሮ ሊሰራ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

የፓርቲዉን አሰራር ስርዓት ማዕከል ያደረጉ የድጋፍና ክትትል ስራዎች በአግባቡ በመምራት ዉጤት እንዲገኝ ሊሰራበት የሚገባዉ ጉዳይ ነዉም ብለዋል፡፡

ለዚሁ ተግባራት ስኬት በቀጣይ ጊዜያት የመፈጸም አቅምን በመገንባት ዉጤት እንዲያስመዘግቡ እንደ ዞን ያለዉን የዉስጥ አቅም ለመፍጠር ተግባራትን በጋራ ማከናወን ተገቢ እንደሆነም አስረድተዋል።

ዘጋቢ፡ አዲስዓለም ታዬ – ከዋካ ቅርንጫፍ