በዘመናዊ የእንስሳት እርባታ ዘርፍ በመሰማራታቸው የቤት ፍጆታን ከማሟላት ባሻገር በኢኮኖሚ ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን በጋሞ ዞን ገረሴ ከተማ በዘርፉ የተሰማሩ አንዳንድ አካላት አረጋገጡ
የወተት ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በከተማው የተጀመረው ዘመናዊ የእንስሳት እርባታ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገረሴ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።
በዘመናዊ የእንስሳት እርባታ በመሰማራታቸው ከቤት ፍጆታ ባለፈ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን በገረሴ ከተማ በዘርፉ ከተሰማሩት መካከል አቶ ተክሉ ቦጋለና ማቲዮስ ቶልባ ይናገራሉ።
የወተት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ያወሱት አርቢዎቹ፤ በቀጣይም የበለጠ ተጠቃሚ እንድንሆን የሚመለከተው አካል ሊደግፈን ይገባል ብለዋል።
አካባቢው ለወተት ልማት ምቹ በመሆኑ በርካታ አርቢዎች በዘርፉ ተሰማርተው መለወጥ እንደሚችሉ የተናገሩት በገረሴ ከተማ ግብርና ዩኒት የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ባለሙያ አቶ ኢሳያስ እዮብ ናቸው።
የሚስተዋለውን የቦታ ጥበትና የመኖ እጥረት ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ጥረት እየተደረገ መሆኑንም በመጠቆም።
የገረሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አዝጌ ካሳ፤ የግብርና ባለሙያዎች በዘርፉ ለተሰማሩ አካላት የተለያዩ ድጋፎችን እያደረጉ እንደሚገኙ አብራርተው፤ በቀጣይም ዘርፉን በተደራጀ መልኩ በመምራት የወተት ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
ዘጋቢ፡ ተመኙህ ገረሱ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
በዘመናዊ የእንስሳት እርባታ ዘርፍ በመሰማራታቸው የቤት ፍጆታን ከማሟላት ባሻገር በኢኮኖሚ ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን በጋሞ ዞን ገረሴ ከተማ በዘርፉ የተሰማሩ አንዳንድ አካላት አረጋገጡ

More Stories
“አስቶን ቪላን ብወደውም ዩናይትድ ታላቅ ክለብ ነው” ዩሪ ቲሌማንስ
የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት የትምህርት ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ግምገማ እና የ2019 ዓ.ም የተማሪዎች ቅበላ የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው
የዳውሮ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 13ኛ ሥራ ዘመን 29ኛ መደበኛ ጉባዔ መካሄድ ጀመረ