ክቡር የሆነውን የሰውን ሕይወት ለመታደግ ደም በመለገስ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ የይርጋጨፌ ከተማ ጤና ጽህፈት ቤት አሳሰበ
በከተማው የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለሚሰጠው የቀዶ ጥገና አገልግሎት ከፍተኛ ድርሻ ያለውን የደም ባንክ ለማስጀመር የሚያስችል የደም ልገሳ ዘመቻ እየተካሄደው ነው፡፡
በወሊድ ምክንያት የሚጎዱ እናቶችን፣ በድንገተኛ ህመምና በተለያዩ አደጋዎች የተጎዱ ወገኖችን ለመታደግ ደም መለገሳቸውን የይርጋጨፌ ከተማ ነዋሪ አቶ ኤልያስ ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡
በይርጋጨፌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የእናቶች እና ወሊድ ክፍል አስተባባሪ አቶ ዮሐንስ ታደሰ፤ ደም መለገስ ከሰብዓዊ አገልግሎቶች አንዱ መሆኑን በመግለፅ በተለይም በወሊድ ወቅት ደም ፈሷቸው ለሚሰቃዩ እናቶች ከፍተኛ ፋይዳ አለው ብለዋል።
ማንኛውም ሰው በህክምና በመመርመር ደም መለገስ እንደሚችል ያነሱት አስተባባሪው፤ ዕድሜው ከአስራ ስምንት አመት ያለፈ፣ ክብደቱ ከሃምሳ ኪሎ ግራም የበለጠ፣ ከደም እና ከደም ጋር ተያያዥ ከሆኑ ህመሞች ነጻ የሆነ ሰው መለገስ እንደሚችል አብራርተዋል።
በወሊድ ምክንያት፣ በድንገተኛ ህመም እና በተለያዩ አደጋዎች ደም ሳያገኙ ለሞት እየተዳረጉ መሆኑን የተናገሩት አቶ ዮሐንስ፤ ማህበረሰቡ በቀላሉ ደም በመለገስ የወገኖቻቸውን ህይወት እንዲታደጉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ክቡር የሆነውን የሰውን ሕይወት ለመታደግ ደም በመለገስ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ያሳሰቡት ደግሞ ደም ሲለግሱ ያነጋገርናቸው የይርጋጨፌ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳዊት ጉሚ ናቸው፡፡
የዲላ ሳትላይ የደም ባንክ ኃላፊ አቶ ታምራት ገረሙ እንደገለፁት፤ በደም እጦት ምክንያት የሚጎዳውን ህይወት ለመታደግ በበጎ ፍቃደኛ ለጋሾች ደም የመሰብሰብ ተግባር እያከናወኑ ነው፡፡
ዘጋቢ: አሀዱ አሸናፊ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
በዘመናዊ የእንስሳት እርባታ ዘርፍ በመሰማራታቸው የቤት ፍጆታን ከማሟላት ባሻገር በኢኮኖሚ ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን በጋሞ ዞን ገረሴ ከተማ በዘርፉ የተሰማሩ አንዳንድ አካላት አረጋገጡ
ለሴቶች ሞት ምክንያት የሆነውን የማህፀን በር ካንሰር ቅድመ ምርመራ በማድረግ መከላከል እንደሚገባ የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል የማህፀንና ፅንስ ሐኪም ዶ/ር አረጋኸኝ ሙሉጌታ አሳሰቡ
7ኛ ዙር ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው