ምክር ቤቶች የህዝብ ሉዓላዊነት መገለጫ በመሆናቸው ለህዝብ ተጠቃሚነት ቅድሚያ ሰጥተው እየሰሩ መሆናቸው ተጠቆመ
በዳውሮ ዞን የዋካ ከተማ አሰተዳደር ምክር ቤት 5ኛ ዙር 2ኛ ሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል፡፡
ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የዋካ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ እስክንድር ተፈራ፤ ምክር ቤቶች የህዝብ ሉዓላዊነት መገለጫ ከመሆናቸውም ባለፈ በአገር ደረጃ የተጀመሩ የለውጥ ጉዞዎችን አጠናክረው በማስቀጠል የህዝብ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ረገድ የበኩላቸውን ሚና እየተወጡ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
በምክር ቤቶች የተከናወኑ ተግባራት አበረታች ቢሆኑም በቀጣይ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም አመላክተዋል።
ለምክር ቤቱ 2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የተቋማት ረፖርት ያቀረቡት የዋካ ከተማ ከንቲባ አቶ ኢያኤል ታደስ፤ በተያዘው በጀት አመት የተሻለ ወጤት መመዝገቡን በመጠቆም በጠንካራ ጎን የተነሱትን በማስቀጠል፣ ደካማ ጎን ያሉትን ማሻሻል እንደሚገባ ገልጸዋል።
በጉባዔው የተነሱ ጉዳዮች በአስፈጻሚው አካላት ዘንድ በቀጣይ ወራት መሻሻል የሚገባቸው እንደሆኑ ተነስቷል።
ከጉባኤው አባላት መካከል ወ/ሮ መሰረት ሲሳይ እና አቶ ዘሪሁን ገበየሁ በጋራ በሰጡት አስተያየት፤ ምክር ቤቱ የህዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በስፋት መወያየቱን አንስተዋል።
ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ከመድረክ በመሥጠትና የቀረቡትን ሹመቶች በማፅደቅ ጉባኤው ተጠናቋል።
ዘጋቢ፡ አንዱዓለም ኡማ – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
7ኛ ዙር ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው
የአለም አቀፉን ተለዋዋጭ ሁኔታ በአግባቡ ለይቶ የሀገር ውስጥ ተጋላጭነትን መቀነስ የሚያስችሉ ሥራዎችን በትኩረት በመስራት የህዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ ገለፁ
ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት እና ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በወልቂጤ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሔደ ነው