ሲዳማ ቡና መቀሌ 70 እንደርታን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ
በ25ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ሲዳማ ቡና መቀሌ 70 እንደርታን 1ለ0 በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል።
ከአመሻሽ 12 ሰዓት ጀምሮ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አቤል ያለው ለሲዳማ ቡና ወሳኟን የማሸነፊያ ጎል አስገኝቷል።
አቤል ያለው በሲዳማ ቡና ማልያ ሦስተኛ የሊግ ጎሉን ነው ያስቆጠረው።
በበጋው የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ሲዳማ ቡናን የተቀላቀለው አቤል ያለው በውድድር ዘመኑ አጠቃላይ 11ኛ የሊግ ጎሉን በማስቆጠር ከፍተኛ ግብ አግቢነቱን እየመራ ይገኛል።
በአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ የሚመራው ሲዳማ ቡና በውድድር ዓመቱ 13ኛ የሊግ ድሉን አስመዝግቧል።
ሲዳማ ቡና ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን 48 በማድረስ ከተከታዩ ሀዋሳ ከተማ በ8 ነጥብ ርቆ ሊጉን ይመራል።
መቀሌ 70 እንደርታ በአንፃሩ በ23 ነጥብ 19ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ዘጋቢ ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ አስፈረመ
ማንቸስተር ዩናይትድ አንድሬ ሳንቶስን አስፈረመ
የ2018 የCBE የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በማሸነፍ ሁለት ዋንጫ ላነሳው የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ክልሉ ያዘጋጀውን የዕውቅናና የሽልማት ፕሮግራም ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 06/2018 ከቀኑ 12፡00 ጀምሮ በሀዋሳ ሀይሌ ሪዞርት ይካሄዳል።