ማንቸስተር ሲቲ ሊቨርፑልን 4ለ0 በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜ አለፈ
በእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ማንቸስተር ሲቲ ሊቨርፑልን 4ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜ አልፏል።
በኤቲሐድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ለማንቸስተር ሲቲ የማሸነፊያ ጎሎች ኤርሊንግ ሀላንድ 3 ጎሎችን በማስቆጠር ሀትሪክ መስራት ሲችል አንቶይን ሴሜንዮ ቀሪዋን ግብ አስገኝቷል።
በጨዋታው ሊቨርፑል የፍፁም ቅጣት ምት አግኝቶ የነበረ ቢሆንም ሞሐመድ ሳላህ መቶት ጀምስ ትራፎርድ አድኖበታል።
ኤርሊንግ ሀላንድ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ለሀገሩ እና ለክለቡ በ50 ጨዋታዎች 46 ጎሎችን አስቆጥሯል።
ማንቸስተር ሲቲ ለስምንት ተከታታይ ዓመታት በእንግሊዝ የኤፍኤ ዋንጫ ለግማሽ ፍፃሜ በመድረስ በራሱ ተይዞ የነበረውን ክብረወሰን አሻሽሏል።
ማንቸስተር ሲቲ ማሸነፉን ተከትሎ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ሲሻገር ሊቨርፑል ከውድድሩ ተሰናብቷል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
አሌክሳንደር አይሳክ ወደ ልምምድ ሊመለስ ነው
አርሰናል የክርስቲያን ኮፋኔን የዝውውር ሁኔታ መከታተል ጀመረ
ፈረንሳይ ስፔንን በመብለጥ በወቅታዊ የሀገራት ደረጃ ቀዳሚ ሆነች