አሌክሳንደር አይሳክ ወደ ልምምድ ሊመለስ ነው
የሊቨርፑሉ አጥቂ አሌክሳንደር አይሳክ ከረጅም ጊዜ በኋላ ወደ ልምምድ ሊመለስ መሆኑ ተገልጿል።
የብሪታንያ የምንጊዜም ውዱ ፈራሚ አሌክሳንደር አይሳክ ካጋጠመው የቁርጭምጭሚት ጉዳት አገግሞ በዛሬው ዕለት ከቡድኑ ጋር ወደ ቡድኑ ልምምድ እንደሚመለስ አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ተናግረዋል።
ስዊዲናዊው አጥቂ በታህሳስ ወር ከቶትንሃም ጋር በተካሄደው ጨዋታ ጉዳት ማስተናገዱ ይታወሳል።
አይሳክ ባጋጠመው ጉዳት የቀዶ ጥገና የተደረገለት ሲሆን ከአራት ወራትም በኋላ ወደ ሜዳ የሚመለስ ይሆናል።
የ25 ዓመቱ የፊት ተጫዋች በመርሲሳይዱ ክለብ የመጀመሪያ ዓመት ቆይታው ከጉዳት ጋር እየታገለ ይገኛል።
አሌክሳንደር አይሳክ ለሊቨርፑል በሁሉም ውድድሮች እስካሁን 16 ጨዋታዎችን ብቻ አከናውኖ 3 ጎሎችን በስሙ አስመዝግቧል።
ሊቨርፑል የፊታችን ቅዳሜ በእንግሊዝ ኤፍኤ ዋንጫ በሩብ ፍፃሜ ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ከቀኑ 8 ሰዓት ከ30 ጀምሮ ይጫወታል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ አስፈረመ
ማንቸስተር ዩናይትድ አንድሬ ሳንቶስን አስፈረመ
የ2018 የCBE የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በማሸነፍ ሁለት ዋንጫ ላነሳው የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ክልሉ ያዘጋጀውን የዕውቅናና የሽልማት ፕሮግራም ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 06/2018 ከቀኑ 12፡00 ጀምሮ በሀዋሳ ሀይሌ ሪዞርት ይካሄዳል።