አርሰናል የክርስቲያን ኮፋኔን የዝውውር ሁኔታ መከታተል ጀመረ
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የባየር ሌቨርኩሰኑን ወጣት አጥቂ ክርስቲያን ኮፋኔን የዝውውር ሁኔታ መከታተል መጀመሩ ተዘግቧል።
ኮፋኔ ከሳምንታት በፊት በተካሄደው በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ሌቨርኩሰን በመድፈኞቹ በድምር ውጤት 3ለ1 በተረታበት ጨዋታ አስደናቂ ብቃቱን ማሳየቱ ይታወሳል።
አሁን ላይ አርሰናል የ19 ዓመቱን ተጫዋች የዝውውር ሁኔታ ማጥናት መጀመሩን ስካይ ጀርመኒ አስነብቧል።
በዘንድሮው የውድድር ዘመን ካሜሩናዊ አጥቂ ክርስቲያን ኮፋኔ በጀርመኑ ክለብ እያሳየ ባለው ብቃት ምክንያት ከአርሰናል በተጨማሪ ሌሎች ትልልቅ የአውሮፓ ክለቦች ለማስፈረም ፍላጎት እያሳዩ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ባየር ሌቨርኩሰን ከተጫዋቾቹ ዝውውር ከ60 እስከ 70 ሚሊዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ እንደሚፈልግ ተመላክቷል።
ክርስቲያን ኮፋኔ በዚህ ዓመት ለባየር ሌቨርኩሰን በሁሉም ውድድሮች 39 ጨዋታዎችን ያከናወነ ሲሆን 7 ጎሎችን አስቆጥሮ 8 ጎል የሆኑ የመጨረሻ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል።
ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ አስፈረመ
ማንቸስተር ዩናይትድ አንድሬ ሳንቶስን አስፈረመ
የ2018 የCBE የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በማሸነፍ ሁለት ዋንጫ ላነሳው የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ክልሉ ያዘጋጀውን የዕውቅናና የሽልማት ፕሮግራም ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 06/2018 ከቀኑ 12፡00 ጀምሮ በሀዋሳ ሀይሌ ሪዞርት ይካሄዳል።