ፈረንሳይ ስፔንን በመብለጥ በወቅታዊ የሀገራት ደረጃ ቀዳሚ ሆነች
የ2018 የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ፈረንሳይ በመጋቢት ወር የፊፋ ወርሃዊ ሀገራት ደረጃ የ2024 የአውሮፓ ሻምፒዮኗን ስፔን በመብለጥ ቀዳሚ መሆን ችላለች።
በአሰልጣኝ ዲዴ ዴሻምፕ የሚመራው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በመጋቢት ወር የሀገራት የጨዋታ ሰሞን በአቋም መለኪያ ጨዋታዎች ሁለቱን የደቡብ አሜሪካ ሀገራት ብራዚልን እና ኮሎምቢያን ማሸነፉ ደረጃውን እንዲያሻሽል አግዞታል።
በአሰልጣኝ ልዊስ ዴላፎንቴ የሚመራው የስፔን ብሔራዊ ቡድን የቀዳሚነት ቦታውን መነጠቁን ተከትሎ ወደ ሁለተኝነት ሲወርድ የወቅቱ የዓለም ሻምፒዮኗ አርጀንቲና በበኩሏ ወደ ሶስተኝነት ዝቅ ብላለች።
እንግሊዝ፣ ፖርቱጋል እና ብራዚል እስከ ስድስት ያለውን ስፍራ ይዘው ተቀምጠዋል።
ሞሮኮ በበኩሏ ከአለም ስምንተኛ እና ከአፍሪካ ቀዳሚ ስፍራ ላይ ተቀምጣለች።
በአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔን በደርሶ መልስ ያሸነፈችው ኢትዮጵያ ከነበረችበት 147ኛ ደረጃ 3 ደረጃዎችን በማሻሻል 144ኛ ደረጃን ይዛለች።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ አስፈረመ
ማንቸስተር ዩናይትድ አንድሬ ሳንቶስን አስፈረመ
የ2018 የCBE የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በማሸነፍ ሁለት ዋንጫ ላነሳው የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ክልሉ ያዘጋጀውን የዕውቅናና የሽልማት ፕሮግራም ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 06/2018 ከቀኑ 12፡00 ጀምሮ በሀዋሳ ሀይሌ ሪዞርት ይካሄዳል።