ስፖርት ህዝባዊ መሠራት እንዲኖረው ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ
ሀዋሳ፡ መጋቢት 21/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ስፖርት ህዝባዊ መሠራት እንዲኖረው ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን እንዲወጣ የዳውሮ ዞን አስተዳደር ጥሪ አቀረበ፡፡
በዞኑ ለ16 ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው ዞናዊ የእግር ኳስ ክለቦች ሻምፒዮና ወድድር በታርጫ ከተማ አስተዳደር ሻምፒዮናነት ተጠናቋል፡፡
በመዝጊያ ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የዞኑ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ደምሴ፥ በዞኑ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በርካታ ክለቦችን ያሳተፈ እግር ኳስ ስፖርት ክለቦች ሻምፕዮና በርካታ ትዝታዎችን፣ ከፍተኛ ስሜትና ፍቅር የተንፀባረቀበት እንደሆነ አውስተዋል።
ይህ ስሜትና ፍቅር ሳይቀዛቀዝ ካስኬድነው የቱሪዝም ኢንዱስትሪ በማስፋፋት የሃብት ምንጭ እንደሚሆንም አረጋግጠዋል።
በእግር ኳስ ጨዋታ የዳኝነትን ስህተትን ጨምሮ በርካታ ክስተቶች እንደሚኖሩ ያስታወቁት የመምሪያው ኃላፊ፥ ይህ ተግባር በሜዳ ላይ ስለሚቀር ቀጣይ እነዚህንና ሌሎችን ያልተገቡ ተግባራት ቀስ በቀስ የእግር ኳስ ስፖርት ማጠናከር እጅግ ተገቢም እንደሆነም አሳስበዋል።
በየዞኑ የተሻለ የእግርኳስ ክለብ እስኪፈጠር ድረስ ጉድለቶችንን እያረምን ከአከባቢያችን አልፈን ለሀገራችንን በእግርኳስ የሚወክሉ ዜጎችን እንፈጥራለን ሲሉ ተናግረዋል።
የዳውሮ ዞን ምክትል አስተዳደርና የዞኑ ስፖርት ምክር ቤት ሰቢሳብ አቶ አስፋው ደሳለኝ በበኩላቸው፥ ስፖርት ለወዳጅነት፣ ለአንድነት፣ ለፍቅር፣ ለመቻቻልና ለአብሮነት መስራት እንደሆነ ተናግረው፥ በተለይ እግርኳስ ልዩ ጥበብ፣ ስፖርታዊ ጨዋነት፣ የቡድን አንድነት እንዲሁም በሜዳ ውስጥ ማሸነፍም ሆነ መሸነፍን በፀጋ መቀበል እንደሆነም አስታውቀዋል።
የተጫዋቾቹ ዲስፕሊን ጉድለት፣ ደጋፊዎች ያሳዩት ያልተገባ አደጋገፍ፣ የዳኝነት ውሳኔ አሰጣጥ ችግርና ሌሎችም ጥቃቅን የስፖርቱን ቤተሰብ የማይመጥን ክስተቶች በ2018 ዓ/ም በዞኑ በእግር ኳስ ክለቦች ውድድር የታዩ ቢሆንም፥ የስፖርት ምክር ቤት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ችግሩን በቶሎ መፍታቲ መቻሉንም አንስተዋል።
የዞኑ ስፓርት ለማጠናከር እንደ አስተዳደር የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እየሰሩ እንደሚገኙ ገልጸው፥ ስፖርት ህዝባዊ መሠራት እንዲኖረው ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን እንዲወጣ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ውድድሩ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ጉልህ ሚና ለተወጡ አካላት የስፖርት ምክር ቤት ስብሳቢው አመስግነዋል።
በዕለቱ ለፍጻሜው ጨዋታ የደረሱት የታርጫ ከተማ አስተዳደርና የዋካ ከተማ አስተዳደር በመደበኛው ሰአት ሳይሸናነፋ በተሰጠው መለያ ምት የታርጫ ከተማ አስተዳደር 3 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት መሆን ችሏል።
በዕለቱ በስታድየም አግኝተን ያነጋገርናቸው የስፖርት ቤተሰቦች፣ ተጫዋቾች፣ የቡድን መሪዎችና ሌሎችም በሰጡት አስተያየት የእግር ኳስ ስፖርት ተወዳጅ ሆኖ እንዲቀጥል ስፖርታዊ ጨዋነት በመላበስ እንዲሁም ስፖርቱን በምንችለው ሁሉ እንደግፋለን ሲሉ አስተያየታቸውን ተሰጥተዋል፡፡
ዘጋቢ፡ አሸናፊ ግዛው – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
የጎፋ ዞን የ2018 ዓ.ም ልዩ ልዩ የስፖርት ሻምፒዮና ውድድር እየተካሄደ ነው
በአፍሪካ ዋንጫ የተሳታፊ ሀገራት ቁጥር ላይ ጭማሪ ተደረገ
አሰልጣኝ ኢጎር ቱዶር ከ44 ቀናት ቆይታ በኋላ ቶትንሃምን ለቀቁ