የጎፋ ዞን የ2018 ዓ.ም ልዩ ልዩ የስፖርት ሻምፒዮና ውድድር እየተካሄደ ነው
በሣውላ ከተማ አዘጋጅነት የሚካሄደው 2ኛው የጎፋ ዞን መላው የስፖርት ሻምፒዮና ውድድር በሣውላ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
የጎፋ ዞን ባህልና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ኒክሰን ለማ በ2ኛው የበጋ ሻምፒዮና በወንዶችና በሴቶች በሁለቱም ፆታ የእግር ኳስ እና የመረብ ኳስ እንዲሁም የአጭርና የረጅም እርቀት የሩጫ ውድድሮች እንደሚካሄዱ ገልፀዋል።
የሣውላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶ/ር ንጉሴ መኮንን በበኩላቸው በመደመር ዕሳቤ እየተጓዝን በመሆኑ ዛሬ የሚጀመረው ስፖርታዊ ውድድር የሚያስተሳስረንና በአንንነት ለዞናችን ሠላም አበክረን የምንሰራበት ነው ብለዋል።
በውድድሩ ማስጀመሪያ የተገኙት የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የስፖርት ምክር ቤት ሰብሳቢ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ ውድድሩ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራትና የእርስ በርስ ግንኙነትን ለማጠናከር የጎላ ጠቄሜታ እንዳለው ገልጸዋል።
የተጀመረው ስፖርታዊ ውድድር በስፖርት ማህበረሰቡ ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅ በመሆኑ ጨዋነትን በተላበሰ መልኩ በሠላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ: አወል ከድር- ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ አስፈረመ
ማንቸስተር ዩናይትድ አንድሬ ሳንቶስን አስፈረመ
የ2018 የCBE የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በማሸነፍ ሁለት ዋንጫ ላነሳው የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ክልሉ ያዘጋጀውን የዕውቅናና የሽልማት ፕሮግራም ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 06/2018 ከቀኑ 12፡00 ጀምሮ በሀዋሳ ሀይሌ ሪዞርት ይካሄዳል።