በ7ኛ ጠቅላላ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ሁሉም ዜጋ የምርጫ ካርድ መያዝ እንደሚገባው ተገለጸ
ሀዋሳ፡ መጋቢት 18/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በመጪው ግንቦት ወር በሚደረገው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ በመራጭነት ለመሳተፍ ሁሉም ዜጋ የምርጫ ካርድ መያዝ እንደሚገባው በባስኬቶ ዞን የሚንቀሳቀሱ ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ።
የዘንድሮ ምርጫ ሁሉም ፓርቲዎች በነፃነት የሚሳተፉበት፣ ነጻና ገለልተኛ የፖለቲካ ምህዳር የታየበት መሆኑን በዞኑ የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቁመዋል።
በባስኬቶ ዞን በ7ኛ ጠቅላላ ምርጫ ለክልልና ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውክልና የሚወዳደሩ በርካታ ፓርቲዎች መካከል ብልጽግና፣ ኢዜማና ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ ተጠቃሽ ናቸው።
ከፓርቲዎቹ አባላትና ዕጩዎች መካከል አንዳዶቹ እንደገለጹልን የምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ገደብ መሠረት በወቅቱ ተመዝግቦ የምርጫ ካርድ መውሰድ ህገ መንግስታዊ መብትን በአግባቡ መጠቀም መሆኑን አስረድተዋል።
ሁሉም ዕድሜው ለምርጫ የደረሰ የትኛውም የዞኑ ነዋሪ በጊዜ ተመዝግቦ የምርጫ ካርዱን እንዲይዝም ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ: አወል ከድር – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ እና የአደረጃጀት ዘርፍ የ2018 በጀት አመት አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዕቅድ ዙሪያ በታርጫ ከተማ ውይይት እየተካሄደ ነው
ኦሞ ባንክ ሳውላ ዲስትሪክት በ2018 በጀት ዓመት ከ86 ሚሊዮን ብር በላይ የተጣራ ቁጠባ ማስመዝገቡን ገለጸ
እየተካሔደ ያለው ሀገራዊ ምክክር በሀገሪቱ አንድነት እና ሠላም ለማስፈን ፋይዳው የጎላ መሆኑን የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ