ምክር ቤቱ በጋሞ ዞን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የ3 ሚላዮን ብር ድጋፍ አደረገ
ሀዋሳ፡ መጋቢት 15/2018 የፌደሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በጋሞ ዞን በመገኘት ተጎጅዎችን አፅናንተው የ3 ሚላዮን ብር ድጋፍ ለዞኑ አስረክበዋል።
እንደዚህ ዓይነት ድንገተኛ አደጋዎች ልብ ሰባሪ ናቸው ያሉት አፈ -ጉባኤው የተጎጂ ቤተሰቦችን ማፅናናትና የተረፉትን መደገፍ ከሁሉም ይጠበቃል ብለዋል።
የፌደራል መንግስት የተጎጂ ቤተሰቦችን በዘላቂነት ለማቋቋም በሚደረገው እርብርብ የበኩሉን እንደሚወጣ ገልፀው ለመጀመሪያው ዙር የ3ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበርክተዋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሴተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የአክለውም ተለያዩ ተቋማት ድጋፋቸውን አሁንም አጠናክረው መቀጠላቸውንና ተጎጂዎችን በዘላቂነት የማቋቋም ሂደቱን አብይ ኮሚቴ በማቋቋም እየተሰራ ነው ብለዋል።
ከችግሩ ስፋት አንፃር በቀጣይም የሚደረጉ ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
ዘጋቢ:- ባዬ በልስቲ
ምክር ቤቱ በጋሞ ዞን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የ3 ሚላዮን ብር ድጋፍ አደረገ

More Stories
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ እና የአደረጃጀት ዘርፍ የ2018 በጀት አመት አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዕቅድ ዙሪያ በታርጫ ከተማ ውይይት እየተካሄደ ነው
ኦሞ ባንክ ሳውላ ዲስትሪክት በ2018 በጀት ዓመት ከ86 ሚሊዮን ብር በላይ የተጣራ ቁጠባ ማስመዝገቡን ገለጸ
እየተካሔደ ያለው ሀገራዊ ምክክር በሀገሪቱ አንድነት እና ሠላም ለማስፈን ፋይዳው የጎላ መሆኑን የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ