ባለፉት ስድስት ወራት የተመዘገቡ ጥንካሬዎችን ለማስፋት፣ ተሞክሮዎችን ለመቀመር እንዲሁም የተስተዋሉ ድክመቶችን ለማረም ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አደጋ ስጋትና ምግብ ዋስትና አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነርና የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት አባል አቶ ወገኔ ብዙነህ በመድረኩ እንደተናገሩት፤ ብልፅግና ፓርቲ ተግባራትን በተገቢው መንገድ እያስፈፀመ ነው ብለዋል።
አያይዘውም በፓርቲው እሳቤ አምስት ቀንን እንደ አንድ ቀን ታሳቢ በማድረግ ፈጥነንና ፈጥረን መስራት ትልቁ ግባችን ነው በማለት ገልፀዋል።
የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዳግማዊ አየለ በበኩላቸው እንደገለፁት፤ ብልፅግና ፓርቲ መንግስት በየጊዜው በየተቋማት የሚያከናውነውን የተግባር አፈፃፀም በበላይነትና በቅንጅት በመምራት ለማህበረሰብ ተጠቃሚነት እንዲያገለግል በማቀድ እና በማስፈፀም ክትትል ያደርጋል ብለዋል።
ከምርጫ ስራዎች ጎን ለጎን መደበኛ የልማት ስራዎችን በትጋትና በፅናት በማከናወን በሁለቱም ተግባራት ውጤት ለማስመዝገብ ርብርብ የሚደረግበት እንደሆነም አብራርተዋል።
የጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጋሻያለው ገላ እንደገለፁት፤ በዞኑ ባለፉት ስድስት ወራት ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት በርካታ ተግባራት መፈፀማቸውን ገልፀዋል።
በበጀት አመቱ ፓርቲውን ለማጠናከር እና ተቋማዊ አሰራርን ለመፍጠር በተሰራው ስራ ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረው፤ በአባላት ንቁ ተሳትፎ ፓርቲውን ለማጠናከር ትልቅ ስኬት መመዝገቡን ገልፀዋል።
የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጋሻያለው፤ በስድስት ወራት የተከናወኑ የፓርቲውን ዋና ዋና ስኬቶችና ቀጣይ መተግበር በሚገባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የውይይት ሰነድ አቅርበዋል።
ዘጋቢ: አወል ከድር – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
ከመማር ማስተማር ተግባር ባለፈ የአካባቢ ማህበረሰብ ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን የሚዛን ግብርና ቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ አስታወቀ
የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ(ዶ/ር) መጭው ጊዜ ከተስፋ ብርሃን ወደሚጨበጥ ብርሃን የምንሸጋገርበት ብሩህ ዘመን መሆኑን ተናገሩ
በተቀሩት አጭር ቀናት ህብረተሠቡ የመራጭነት ካርዱን በመውሰድ የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳና አካባቢው የፌደራልና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጥሪ አቀረቡ