የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ፍቅሬ አማን ከኮንታ ዞን ከተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በአማያ ከተማ ህዝባዊ ውይይት እያካሄዱ ይገኛል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ዞኖች እያካሄዱ ያለው የትውውቅና የልማት ጉብኝት አካል የሆነ ውይይት ነው በኮንታ ዞን አማያ ከተማ በመካሄድ ላይ የሚገኘው።
በዞኑ በመሰራት ላይ የሚገኙ ልዩ ልዩ የልማት ስራዎች ምልከታ በትናንትናው እለት የተካሄደ ሲሆን አነዚህ የልማት ስታዎች ግብረ መልስ ላይ ትኩረት ያደረገ ህዝባዊ ውይይት ነው የሚካሄደው።
ለህዝቡ ቅርብ በመሆን የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ጆሮ ሰጥቶ በማድመጥ ምላሽ መስጠት አንዱ የመደመር መንግስት መገለጫ መሆኑን ከግምት ያሰገባ ውይይት መሆኑን ከተቀመጠው መርሐ ግብር ላይ መረዳት ተችሏል።
በአማያ ከተማ አስተዳደር እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ ህዝባዊ ውይይት የህዝቡን ጥያቄዎች በመስማት በርዕሰ መስተዳደሩ እና በክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣል ተብሎም ይጠበቃል።
ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከቦንጋ ማስተባበሪያ

More Stories
የመደመር መንግስት አሳታፊ የሆነ የልማት ተግባራትን እያከናወነ የህዝብን የመልማት ጥያቄዎች እየመለሰ ይገኛል – የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ፍቅሬ አማን
በዱራሜ ከተማ አስተዳደር የዶክተር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል እየተሰጠ ባለው አገልግሎት ደስተኞች መሆናቸውን አንዳንድ የሆስፒታሉ ተገልጋዮች ተናገሩ
የመደመር መንግስት የህዝብን ጥያቄ በማድመጥ ምላሽ መስጠትን መነሻ ያደረገ የውይይት መድረክ በታርጫ ከተማ እየተካሄደ ነው