የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ጋር በመመተባበር የቃል ኪዳን ቤተሰብ ምስረታ አካሂዷል።
የጋሞ አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች መርሃ-ግብሩን በምርቃት ያስጀመሩ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኢ/ር አብደላ ከማል የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው የቃል ኪዳን ቤተሰብ ምስረታ ዓላማ በአርባምንጭ ከተማ ማህበረሰብና ተማሪዎች መካከል ጥብቅ ግንኙነት በመፍጠር በትምህርትና ስልጠና የበቁ ዜጎችን መፍጠር ነው ብለዋል።
የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ ዶ/ር መስፍን መንዛ በመርሃ-ግብሩ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ተግባሩ ትልቅ ሀላፊነት በመሆኑ በጋራ እንወጠዋለን ብለው ህብረ ብሔራዊ አንድነትን የሚያጠናክር ስምምነት እንደሆነም ገልፀዋል።
የሠላም ሚኒስቴር ተወካይ ወ/ሮ ዮዲት ከበደ የሠላም ዋጋ የላቀ ስለሆነ ዘላቂ ሠላም ለማምጣት የቃል ኪዳን ቤተሰብ ትስስር የላቀ ፋይዳ መኖሩን ተናግረዋል።
በልጆች ላይ ዛሬ የሚዘራው ዘር ነገ በመልካም ጤንነትና ውጤት እንዲመለሱ ከማድረጉም በላይ የተጠማነውን ሠላም ለማግኘት ይረዳል ብለዋል።
በዩኒቨርሲቲው ፖለቲካል ሳይንስ መምህር የሆኑት ተፈራ ቃኛለው በማህበረሰቡና ተማሪዎች መካከል ጥልቅ ትስስር በማስፈን እና ምቹ የሆነ የትምህርት እና ስልጠና ከባቢ በመፍጠር ውጤታማ የሆኑ ተማሪዎችን ማፍለቅ የፕሮግራሙ ዋና ዓላማ እንደሆነ አብራርተዋል።
ከቃል ኪዳን ተማሪዎች መካከል ቤተልሄም ባልቻ መርሃ -ግብሩ በዩኒቨርስቲው በመጀመሩ መደሰቷን ተናግራ ለአንድነትና ለሠላም ትልቅ ጥቅም ይኖረዋል ነው ያለችው።
ከቃል ኪዳን ቤተሰብ መካከል ዶ/ር ተክሉ ወጋየሁ በተቀበሉት ሀላፊነት ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረው የተጣለባቸውን ኃላፊነት በፍፁም ቅንነት እንደሚወጡ ገልፀዋል።
ወላጅና ቤተሰብ በመጣመር ውል ከተፈራረሙ በኃላ መርሃ-ግብሩ በብሔራዊ መዝሙር መቋጫውን አግኝቷል።
ዘጋቢ: ተነሳ ተረፈ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
በክልሉ የሚገኙ ነዋሪዎችን ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥራ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ገለጹ
የእናቶችንና ጨቅላ ህፃናትን ሞት ለመቀነስ በሚደረጉ ጥረቶች ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳደር (ዶ/ር ) እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ምርቃትና የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ-ስረዓት እየተካሄደ ይገኛል