4ኛው ዙር የልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) መከላከያ ክትባት ዘመቻ ከታህሳ 3-6 ለአራት ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ታሕሣሥ 01/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) 4ኛው ዙር የልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) መከላከያ ክትባት ዘመቻ ከታህሳ 3-6 ለአራት ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
ክትባቱ ለ1 ነጥብ 5 ሚሊዬን በላይ ህፃናት የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አጉኔ አሾሌ እንደገለፁት 4ኛው ዙር የልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) መከላከያ ክትባት ዘመቻ ከታህሳ 3-6 ለአራት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ሲሆን ክትባቱ ለ1 ነጥብ 5 ሚሊዬን በላይ ህፃናት ተደራሽ ይሆናል ብለዋል።
አክለውም ቤት ለቤት በሚሰጠው የፖልዮ ክትባት ዘመቻ ለማሳለጥ አስፈላጊ ግብአቶችን በማሟላት ዝግጅቱ መጠናቀቁን ገልጸዋል።
በዘመቻ ወቅት በክልሉ በቅርቡ የተከሰተውን የማርበርግ ቫይረስ ምልክት ያለባቸውን መለየት፣ የወባ በሽታና በሌላም በሽታ ታመው ቤት የተኙ ካሉ መለየትና ወደ ህክምና ተቋም የመውሰድ ስራ እንደሚሰራ አብራርተዋል።
በዚህ ዘመቻ ወቅት በሚደረገው ልየታ ከ1 አመት በታች ክትባት ያልጀመሩም ሆነ ጀምረው ያቋረጡ ህፃናት የሚከተቡ መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልፀው፥ ዘመቻው የተሳካ እንዲሆን የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሁሉም አካል ተሳታፊ በመሆን ህፃናትን ከልጅነት ልምሻ ለመከላከል ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ: ገነት መኮንን – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
የመስቀል እና የደመራ በዓልን ስናከብር ኢየሱስ ክርስቶሰ በመስቀል ላይ የከፈለውን የደም ዋጋ በማሰብ ሊሆን ይገባል ሲሉ የወላይታ ዞን የኃይማኖት አባቶች አሳሰቡ
የመስቀል በዓልን ስናከብር የተቸገሩትን በመርዳትና ለሀገር ሰላም ዘብ በመቆም ሊሆን ይገባል – መጋቤ ሰናያት ያዕቆብ ደስታ
በበዓል ምክንያት በምርቶች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ አቅማቸውን እየፈተነ በመሆኑ የሚመለከተው አካል ገበያውን እንዲያረጋጋ ያነጋገርናቸው የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ