በጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳና ላሃ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የብልፅግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ለፓርቲው የ1 ሚሊዮን 400 ሺህ ብር ድጋፍ አበረከቱ
ፓርቲው እያከናወነ የሚገኘው ሁለንተናዊ የሐገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ግቡን እስኪመታ የተጀመረው ድጋፍ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑም ተመላክቷል።
የጎፋ ዞን ላሃ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አሸናፊ ጮራ በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ሶስት ቀጠናዎችን በማስተባበር 190 ሺህ ብር የሚገመት እያንዳንዳቸው አንድ አንድ በሬ እንዲሁም 20 ሺህ ብር ጥሬ ገንዘብ ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል።
የመሎ ኮዛ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙሉነህ አውሳቶ በበኩላቸው በወረዳው የሚገኙ ሁሉንም ቀበሊያት በንቅናቄ በማሳተፍ በጥቂት ግዚያት 10 በሬዎችና በጥሬ ገንዘብ 716 ሺ ብር ማበርከት መቻሉን ገልጸዋል።
በርክብክቡ ላይ የተገኙት የጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኋላፊ አቶ ቦረና ቦላዶ በዞኑ ከሚገኙ 188 ሺ 441 የብልግና ፓርቲ አባላት ከ89 ሚሊዮን ብር በላይ ሀብት ለመሠብሰብ እቅድ የተያዘ መሆኑን ገልጸው በየመዋቅሩም የተሻለ አፈጻጸም እየተዘገበ ይገኛል ብለዋል።
ጠንካራ መንግስትና ሐገር ለመገንባት የገዢውን ፓርቲ በአባላቱ በጎ ፍቃደኝነት በሚገኝ ድጋፍ የፋይናን አቅሙን ማደራጀት አስፈላጊ መሆኑንም አቶ ቦረና አብራርተዋል።
የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የሥራና ክህሎት መምሪያ ኋላፊ አቶ ምናሴ ኤልያስ አባላቱ በመደበኛው መዋጮ ከሚያደርገው ድጋፍ ባሻገር በልዩ ሁኔታ ስጦታዎችን በማበርከት ለፓርቲው የሚያሳየው ውግንና ተጠናክሮ የሚቀጥል ነው ብለዋል።
ከግዜ ወደ ግዜ እንደ እንደ ሐገር ብሎም በክልሉ ፓርቲው በመደበኛ ሥራዎችና እኒሼቲቮች እያስመዘገበ የሚገኘው ውጤታማነት አባላቱ ዘንድ ከፍተኛ መነቃቃትን መፍጠሩንም አቶ ምናሴ አክለው አብራርተዋል።
ዘጋቢ: አወል ከድር – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
3ኛው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የክለቦች ሻምፒዮና የምድብ ድልድል ይፋ ሆነ
በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ተገቢውን ትኩረት መስጠትና ተግቶ በመስራት ከድህነት መውጣት ይገባል – ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
ኢትዮጵያን ለዘመናት ከቆየችበት ቁስል ለማላቀቅ ባለፉት የለውጥ አመታት በርካታ ፖለቲካዊ ተግባራት ማከናወኑን መቻሉ ተገለጸ