በኢንቨስትመንት መስክ የተሰማሩ ባለሀብቶች የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በማሳደግ የድርሻቸውን እየተወጡ እንደሚገኝ ተገለጸ
በኢንቨስትመንት መስክ የተሰማሩ ባለሀብቶች የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በማሳደግ የድርሻቸውን እየተወጡ እንደሚገኝ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ታሕሣሥ 01/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በኢንቨስትመንት መስክ የተሰማሩ ባለሀብቶች የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በማሳደግ የድርሻቸውን እየተወጡ እንደሚገኝ በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ አስተዳደር ገለጸ።
በወረዳው በዘርፉ የተፈጠረላቸው ምቹ የስራ ዕድል በመጠቀም የገቢ አቅማቸውን በማሳደግ ላይ መሆናቸውን አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል።
የእኖር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መብራቱ ተክሌ እንደገለጹት መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራባቸው መስኮች አንዱና ዋንኛው የኢንቨስትመንት ልማት መሆኑን ጠቁመው፥ በወረዳው በመስኩ የተሰማሩ ባለሀብቶች የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በማሳደግ ረግድ የድርሻቸውን እየተወጡ እንደሚገኝም አብራርተዋል።
በወረዳው 13 የሚሆኑ ባለሃብቶች ከ10ሺ ሄ/ር በላይ መሬት ተረክበው በግብርናው መስክ ተሰማርተው እየሰሩ እንደሚገኝ ዋና አስተዳዳሪው ገልጸው፥ ወደ ውጭ የሚላኩ የኤክስፖርት ምርቶች ለማሳደግና ከውጪ የሚገቡትን ምርቶች ለመቀነስ ባለሀብቱ ከዚህ በፊት በወረዳው ተመርተው የማይታወቁ የቅባት እህሎች በስፋት እያመረቱ መሆኑንም ተናግረዋል።
ከዚህ በተጓዳኝ ባለሃብቶቹ በቴክኖሎጂ የታገዘ የእርሻ አሰራር ዘዴን ለአካባቢው አርሶአደር በማስተዋወቅ ለበርካታ ስራ አጥ ወጣቶች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል እየፈጠሩ እንደሆነም አመላክተዋል።
በግብርናው ዘርፍ የምርጥ ዘር በማምረት የሃገሪቱ የምርጥ ዘር አቅርቦት እጥረትን ለመቅረፍ ባለሀብቱ የድርሻቸውን እየተወጡ እንደሚገኝ ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል።
በቀጣይም በወረዳው ያለውን ውስን የመሬት ሀብት በተሻሻለ የግብርና አሰራር ዘዴ ተጠቅመው ለማምረትና በእንስሳት እርባታው ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች ወረዳው ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር እንደሚችል አቶ መብራቱ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በወረዳው ሻፋሞ ቀበሌ የሚገኘው “የኤታኸሎ የእርሻ ልማት ድርጅት” ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ታደለ ደርሶ ድርጅቱ ከተቋቋመበት 2010 ዓ.ም ጀምሮ 60 ሄ/ር መሬት በመጠቀም በርካታ የግብርና ስራዎችን በማከናወን በሃገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ላይ የድርሻውን እየተወጣ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
በ2017/18 የምርት ዘመንም የበቆሎ፣ የጤፍ፣ የበርበሬና የኑግ ምርጥ ዘር በማምረት እንዲሁም የግብርና ተረፈ ምርቶችን በመጠቀም እንስሳትን በማርባት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
ድርጅቱ ለ10 ለቋሚና 200 ለሚሆኑ ወጣቶች ጊዜያዊ የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉን አቶ ታደለ አክለዋል።
በስፍራው አግኝተን ያነጋገርናቸው የስራ ዕድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች በሰጡት አስተያየት ከድርጅቱ በሚያገኙት ገቢ የኢኮኖሚ አቅማቸውን ማሳደግ መቻላቸውን ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡ ፉኣድ አብደላ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
በጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳና ላሃ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የብልፅግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ለፓርቲው የ1 ሚሊዮን 400 ሺህ ብር ድጋፍ አበረከቱ
የፖሊዮ ክትባት ዘመቻን በተመለከተ ለጤና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
የደረሱ ሰብሎችን የቤተሰብ ጉልበትና የልማት ቡድን አደረጃጀት በመጠቀም በመሰብሰብ ላይ መሆናቸውን በጠምባሮ ልዩ ወረዳ የባዳ ቀበሌ አርሶ አደሮች ተናገሩ